ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ግዜ ጥቅምት 9 /2012 : ጨረታዉ የሚዘጋባት ቀን እና ሰዓት በ30ኛዉ ቀን 4:00 ሰዓት : ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት በ30ኛዉ ቀን 4:30 ሰዓት
- የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድና የአቅራቢዎች መታወቂያ ፍቃድ ያላቸው
- ቫት የተመዘገቡና የመጨረሻ ወር ቫት ዲክለር ያደረገ ቲን ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታው ዶክመንት የማይመለስ 200(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መቐለ ውሃ አግልግሎት ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታው ዶክመንት ከደጋፊ ስራ ሂደት ግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላሉ ።
- የጨረታ ዶክመንቱ ማስገባት የሚቻለው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ወደ ጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚዘጋው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4:30 ሰዓት ተጫራች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ሁሉም ተጫራቾች 50,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በcpo፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የቀረበ ዋስትና፣ ጥሬ ገንዘብ፣ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትእዛዝ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የተጫራቹ ነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪም በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው መቅረብ አለባቸው።
- በዶክመንቱ ከተሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ ውል ማስከበሪያ ካሽነፈው ዋጋ በCPO፣ በተረጋገጠ የባንክ ጋራንቲ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የውል ማስከበርያ (Performance bond guarantee) 10% ማስያዝ የሚችልና በ3 ቀን ውስጥ ውል አስሮ በዶክመንቱ በተጠቀሰው ቀን ንብረቱን ማስገባት የሚችል
- በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛበት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግስት ግዢ እንዳይሳተፍ ለማድረግ ወደ ክልሉ ፋይናንስና ፕላን ቢሮ ደብዳቤ እንደምንፅፍ ፣
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣውን የጨረታ ዶክመንት ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታውፀንቶ የሚቆየውጨረታውከተከፈተ ለ60 ተከታታይ ቀናት ብቻ ነው፡፡
- ጽ/ቤቱ ጨረታው እንደ አስፈላጊነቱ ከእያንዳንዱ ነጠላ ዋጋ በ20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የሚቀርበው ጨረታ ዶክመንት
- 14.1. ቴክኒካል አንድ አርጅናልና ሁለት ኮፒ ሰነድ ለየብቻው አሽጎ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም
- 14.2. ፋይናንሺያል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ሰነድ ለየብቻው አሽጎ ማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል።
- ጽ/ቤቱ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፦0344407335 /0914755845
አድራሻ ፡- ትግራይ መቐለ
የመቐለ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
Company Info
መመለስ