የጨረታ ማስታወቂያ
በትግራይ በሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዉሃ ሃብት ቢሮ ለቢሮኣችን ኣገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የኬሚካል ሪኤጀንቶች በግልፅ ጨረታ ኣወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
በዚህ መሰረት የሚቀጥለዉ መስፈርት የሚያማሉ መወዳደር ይችላሉ
1 ማንኛዉ በዘርፉ የተሰማራና ብቃት ያለዉ ድርጅት ከላይ የተዘረዘሩትነ እቃዎች ለማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል::
2 ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከ 29/10/2007 ጀምሮ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ከዚሁ በታች ከተጠቀሱት ኣድራሻዎቻችን ማግኘት ይችላሉ::
3 የጨረታ ሰነዳችን ጨረታዉ ሬድዩ ፋና ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተካታታይ 15 ቀናት ከታች በተገለፀዉ ኣድራሻችን በመቅረብ ማግኝት ይቻላል::
4 ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ቫት ዲክለረሽን የኣቀራቢነት መለያ ካርድ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN NUMBER) ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
5 ተጫራቾች ብር 10,000 (ኣስር ሺ ብር) የጨረታማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ (CPO ) ወይም የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባችዋል::
6 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸዉን “በሁለት ፖስታ “ኣንድ “ኦርጅናል “እና ኣንድ “ኮፒ” ፋይናንሻልና ቴክኒካል ለየብቻዉ በስም የታሸጉ ኢንቨሎፖች እስከ ቀን 17 /11/ 2007 ዓም ከቀኑ 9:00 ከሰዓት በሃላ በፊት ከላይ በተጠቀሰዉ የ ኣድራሻ በተዘጋገዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ::
7 ጨረታዉ በተመሳሳይ ቀን 17/11 /2007 ዓ/ም ከቀኑ 9:30 ከሰዓት በሃላ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በቢሮ መደበኛ ግዥ ክፍል ይከፈታል በተጨማሪ ተጫራቾች ስለ ጨረታ ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 0342410135 /0344411794/05 በተጠቀሰዉ ኣድራሻ ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ::
8 ይህ ጨረታ የሚቆይበት ጊዜ(Bid Validity Period) ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለ45 የስራ ቀናት የፀና ይሆናል
9 መስረቤቱ የተሻለ ኣማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በክፋል ወይም በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
የትግራይ በሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዉሃ ሃብት ቢሮ መደበኛ ግዥ ክፍል
ንተወሳኪ ሓበሬታ ብስልኪ ቁፅሪ 0344411794/ 95 ብምድዋል ምሕታት ይከኣል እዩ
መመለስ