ለ 3ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
መቀሌ ዉሃ አገልግሎት ጽቤት የ 2007 ዓ/ም የሚገለግል Physical Verification , Listing and Valuation of all Assets / አሴት ቫሌሽን / ለማሰራት ሰለሚፈልግ በግልፅ የጨረታ ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች ጥሪዉን ያቀርባል
በዚህ መሰረት መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች
የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የአቅራቢዎች መታወቂያ ያላቸዉ::
ቫት የተመዝገበና መጨረሻ ወር ቫት ዲክለር ያደረገ ቲን ቁጥር ያለዉ::
የጨረታ ዶክመንት የማየመለስ 100 / አንድ መቶ ብር /በመክፈል ከመቐለ ዉሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ከ 2 /3/ 2007 ዓ/ም እስከ 22 /4/ 2007 ዓ/ም ባለዉ ጊዜ ዉስጥ በመቐለ ዉሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ከግዥ ፋይናንስን ንብረት አሰተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 13 መግዛትና በተዘጋጀዉ ሳጥን ማሰገባት ይችላሉ::
በተመሳሳይ ቀን 22 /4/ 2007 ዓ/ም ከጠዋቱ 3 :00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታ ሳጥኑ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል::
ሁሉም ተጫራቾች 5, 000 / አምስት ሽህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ CPO መልከ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::
ጨረታዉ በሰም በታሸገ ፖስታ የጠቅላላ ዋጋ በግልፅ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪም በጨረታ ዶክመንቱ ዉስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተዉና ተፈርመዉ መቅረብ አለባቸዉ::
በደኩመንት ከተሰጠዉ ስፐስፊኬሽን ዉጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለዉም::
የጨረታዉ አሸናፊ ዉል ማሰከበሪያ ካሸነፈዉ ዋጋ CPO በተረጋገጠ የባንክ ጋራንቲ 10 % ማስየዝ የሚችል በ 5 ቀን ዉስጥ ዉል አስሮ በ 90 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ንብረቱን ማቅረብ የሚችል ና ለእታዉ ጥራት ለአንድ ዓመት ዋስትና መስጠት የሚችል ::
በጨረታዉ ሂደት ጨረታወን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ እንደሚሆንና በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ እነደሚደረግ::
ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በሃላ የሚመጣዉን የጨረታ ዶክመንተ ተቀባይነት የለዉም የጨረታ ዋጋዉ ፀንቶ የሚቆየዉ ጨረታዉ ከተከፈተ ለ 45 የስራ ቀናት ብቻ ነዉ::
አሸናፊዉ ያሸነፈዉን ስራ በዶኩመነቱ በተቀመጠዉ ጊዜ ሰርቶ ለጽ / ቤታችን ማስረከብ የሚችል::
ጽ/ ቤቱ ጨረታዉ በ 25 % የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
የጨረታዉ ዶክመንተ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ለየብቻዉ አሽጎ ማቀረብ የሚችል መወዳደር ይችላል በታዘዘዉ መሰረት ካለቀረበ ግን ዉድቅ ይሆናል::
አድራሻ ትግራይ መቐለ
ቀበሌ 03
መቐለ ዉሃ አገልግሎት ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 13
ስልክ ቁጥር +251 0344 40 73356
ፈክስ ቁጥር 0344400911 / 0344410000
መመለስ