- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ
- ጫራቾች በጨረታ ለማሳተፍ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡትእቃዎች ዝርዝር መግለጫ ወይም አስፈላጊውን መረጃ ማያያዝ እንዲሁም የእቃውን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 06 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወደደሩበት የእቃውን ማለትም ከ15%ቫት በፊት ካለው ጠቅላላ ዋጋ 1%አንድ ከመቶ/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን አንድ ወጥ በሆነ ኤንቨሎፕ፣ አንድ ኦርጅናል /2/ ሁለት ቅጅዎችን በሚገባ በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጥር 22 እስከ የካቲት 6 |2012ዓ.ም ሰዓት 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ ቤቱ የመዝናኛ ክበብ የካቲት 6/ 2012 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች ስለጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አፋር ውሃ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይይሬክተር ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 666 00 44 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 033 666 04 00 በመልክ ማግኘት ይችላሉ፡፡ .
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የውሃ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ
መመለስ