ስለዚህ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር ከፍሎ መግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
ተቁ | የመሣሪያው ዓይነት | የመለያ ቁጥር | ብዛት | |
1 | Lathe Machine | CS6266C | 1 | |
2 | Hydraulic Plate Bending Machine | WC67Y | 1 | |
3 | Drill Press | ZJ5132 | 1 | |
4 | Hand Bending Machine | WHO6-2.5*2500 | 1 | |
5 | Drilling and Milling Machine | ZX6350C | 1 | |
6 | Rolling Machine | WLLGL.5*1300 | 1 | |
7 | Aluminum Hand Cutter | CSB315 | 1 | |
ንብረቶቹን ከመቀሌ ከተማ በግምት ወደ 9 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ አዲስ በመገንባት ላይ ካለው የአውቶቡስ ተራ አጠገብ ካለው የድርጅታችን የመቀሌ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር ጠዋት ከ 3፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የሚፈልጉትን ዕቃ ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ፎርም ላይ በመሙላትና ለጨረታ ማስከበሪያም ያቀረቡትን ዋጋ 10 በመቶ በCPO ብቻ በማስያዝ የድርጅቱ የመቀሌው ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ከአስር ተከታታይ ቀናት በኋላ በሚኖረው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመቀሌ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ስልክ ቁጥር፡- 0114-421133 የውስጥ መስመር 212 ወይም መቀሌ 034-44-10696/0914 -310978 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር
መመለስ