የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የመቐለ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2017 በጀት አመት የሚያገለግል የውሃ ማጣርያ ኬሚካል (ክሎሪን) ግዢ አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ስለፈለገ በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች ጥሪውን ያቀርባል
1. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድና የአቅራቢዎች መታወቂያ ፍቃድ ያላቸው
2. ቫት የተመዘገበና የመጨረሻ ወር ቫት ዲክለር ያደረገ ቲን ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ
3. የጨረታው ዶክሜንት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) በመክፈል መቐለ ውሃ አግልግሎት ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታው ዶክሜንት ከደጋፊ ስራ ሂደት ግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር G1_02 መግዛት ይችላሉ
4. የጨረታ ዶክሜንቱን ማስገባት የሚቻለው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 2017 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ወደ ጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይችላሉ።
5. ጨረታው የሚዘጋው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 2017 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ተጫራች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እሁድ ወይም የህዝባዊ በአል ከሆነ ደግሞ ቀጥሎ ባለው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ተጫራች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ሁሉም ተጫራቶች 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበርያ በጥሬ ገንዘብ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክረዲት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል
7. ተጫራቹ ነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪም በጨረታ ዶክሜንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው መቅረብ ኣለባቸው።
8. በዶክሜንቱ ከተሰጠው ስፐስፍኬሸን ውጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም።
9. የጨረታው አሸናፊ ውል ማስከበርያ ካሸነፈው ዋጋ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ዋስትና የውል ማስከበርያ (Performance bond guarantee) 10% ማስያዝ የሚችልና በ3 ቀን ውስጥ ውል አስሮ በዶክሜንቱ በተጠቀሰው ቀን ንብረቱን ማስገባት የሚችል
10.በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛበት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግስት ግዢ እንዳይሳተፍ ለማድረግ ወደ ክልሉ ፋይናንስና ፕላን ቢሮ ደብዳቤ እንደምንፅፍ
11. ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣው የጨረታ ዶክሜንት ተቀባይነት የለውም።
12. ጨረታ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተ ለ40 ተከታታይ ቀናት ብቻ ነው።
13. ጽ/ቤቱ ጨረታው እንደ አስፈላጊነቱ ከያንዳንዱ ነጠላ ዋጋ በ20% የመጨመር ወይም የመተነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. የሚቀርበው ጨረታ ዶክሜንት
14.1 ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ሰነድ ለየብቻው አሽጎ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም
14.2 ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ሰነድ ለየብቻው አሽጎ ማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል።
15.ፅ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊር የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ - ትግራይ መቐለ
መቐለ ውሃና ፍሳሽ አገልገሎት ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 034 440 7335/09 14 755 845