በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የመቐለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት ተይዘው ውርስ የተደረጉ በርበሬና ቅመማ ቅመም፣የእህል ምርት ውጤቶች ፣ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች ማጫወቻ እና የንፅህና የማስዋቢያ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልዕ ጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል፡፡
ፈጣን የአይአይ ማጠቃለያ
generated by ai* ተፈላጊ ሰነዶች እና ማስከበሪያ፡ የፀና ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የግብር ክሊራንስ፣ ግምታዊ ዋጋቸው ከ500,000 ብር በላይ ለሆኑ ዕቃዎች የVAT ምዝገባ ሰርቲፊኬት እና የጨረታ ዋጋን 5% የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
* የሰነድ ሽያጭ እና ዕቃዎች ምልከታ፡ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 ብር በመክፈል ከ18/02/2019 ዓ.ም እስከ 26/02/2019 ዓ.ም በሥራ ሰዓት መግዛት እና የዕቃዎችን ናሙና በጽ/ቤቱ በአካል ተገኝቶ መመልከት ይቻላል።
* የጨረታ መዝጊያ እና መከፈቻ ጊዜ፡ ጨረታው በ26/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ተዘግቶ በዕለቱ በ7፡45 ሰዓት በመቐለ ቅ/ፅ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ (4ኛ ፎቅ) ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
የግልጽ ጨረታ ሰነድ ቁጥር-03/2019
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የመቐለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት ተይዘው ውርስ የተደረጉ በርበሬና ቅመማ ቅመም፣የእህል ምርት ውጤቶች ፣ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች ማጫወቻ እና የንፅህና የማስዋቢያ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልዕ ጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል፡፡
1. በመሆኑ ቅ/ጽ/ቤቱ ባወጣው የዕቃ ሽያጭ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያማሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ሀ) በዘርፉ የፀና ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርቲፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ የምስክር ወረቐት /ክሊራንስ/ ከጨረታ ሰነዱ አያይዞ በፖስታ በማሽግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖሩበታል፡
ለ) የዚህ አንቀጽ ፊደል ተራ (ሀ) ድንጋጌ ቢኖሩም ግምታዊ ዋጋ ከብር 500ሺ በታች የሆነ ማንኛውም ዕቃ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሒሳብ ቁጥር 1000012078537 በመክፈል ደረሰኝ ከጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 104 እንዲሁም የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 411 በመምጣት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን 18/02/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 26/02/2019ዓ/ም መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል በመሄድ ሰነዱ መግዛት ይቻላል፡፡
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት 18/02/2019ዓ/ም ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 26/02/2019ዓ /ም ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መመዝገብ እና ለጨረታ የቀረበ· ዕቃዎች ናሙና በጽ/ቤቱ በአካል እየሄዱ መመልከት ይችላሉ፡፡
4. ጨረታው የሚካሄደው 26/02/2019 ዓ/ም ከቀኑ 7፡30 (ሰባት ሰዓት ከሳላሳ ደቂቃ) ተዘግቶ በዕለቱ ሰባት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ)7፡45 ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደርባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ(5%) የጨረታ ማስከበሪያ በቅ/ጽ/ቤቱ ስም Ethiopia Customs Commission Mekelle Branch office በሚል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰርተው ማስያዝ ይጠበቅባችል፡፡
6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመቀሌ ቅ/ፅ/ቤት የመሰብሳብያ አደራሽ 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ይካሄዳል፡፡
7. ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና የጨረታ ውጤት በተገለጸው በ3 (ሰሶት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላችዋል፡፡
8. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸለት ጊዜ ጀምሮ በ5(አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ዕቃ ዋጋ ገበ, በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡
9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የዕቃው ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃው በሁለት ወር ውስጥ ካልወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል፡
10. በጨረታ የሚሸጠው በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የዕቃዉ አስመጪ ፤ ወኪል፤ ባለቤት ወይም ቤተሰብ በማንኛውም መልኩ በጨረታ መሳተፍ አይችልም፡፡
11. ቅ/ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ሊሰርዝ ይችላል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መቐለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት +251342407107 ወይም +251342408513/ በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑ እንገልፃለን፡፡