ጨረታ ቁጥር 10/2011
የትግራይ ክልል ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ከዚህ በታች የተጠቀሱት የተለያየ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ማለትም፡-
- ሎት 1. የመኪና ዘይትና ቅባት ለ2ኛ ጊዜ የወጣ
- ሎት 2. የእርሻ መገልገያ መሣሪያዎች
- ሎት 3. የጽህፈት መሣሪያዎች
- ሎት 4. የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት 5. የቢሮ ዕቃዎች/ፈርኒቸር/ ለ2ኛ ጊዜ የወጣ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታውለመሳተፍ የምትፈልጉ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እየጋበዝንየተዘጋጀው የጨረታዶክመንት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00/ በመክፈል ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳችሁን በመያዝ ከቢሮአችን የዕቃ ግዥክፍል ቢሮ ቁጥር 12 በሥራ ሰዓት እየመጣችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጩረታው ለመሳተፍ ቀጥለው የተዘረዘሩትን ማሟላትያስፈልጋል፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ አቅራቢዎች ምዝገባ ሠርተፊኬት፣የቫት ሰርተፈኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) እና ያለፈውወር ቫት ዲክለር የተደረገበት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን በጥንቃቄ አይተው መወዳደርአለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በጨረታ ዶክመንቱ ላይ የተጠቀሰው መጠን ገንዘብ በሲፒኦ አሠርተው ጨረታው ከመከፈቱበፊትአያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ቢሮአችን በጨረታ ከቀረበው የዕቃዎች ብዛት እሰከ 20% የመጨመርወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮአችን የዕቃ ግዥ ክፍል ይከፈታል፡፡
- ቢሮአችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 0344403663/0344404346 ወይም በፋክስ ቁጥር 0344409971 /0344403663 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መመለስ