ለኪዳነ ተክለ እና ዘርኡ አብርሃ ሕ/ሽ/ማሕበር ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የተያዘውንና በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 98/90 እና 216/92 የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የተበዳሪው / የመያዣ ሰጪው ስም/ | የሚሸጠው ንብረት ዓይነት | ጨረታው የሚከናወንበት ቦታ | የጨረታው ደረጃ | የጨረታው መነሻ ዋጋ /በብር/ | ጨረታው የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት |
ኪዳነ ተክለ እና ዘርኡ ኣብርሃ ሕ/ሽ/ማሕበር | ሞዴል NPR71፣35 ኩንታል የሚጭን አይሱዙ ተሽከርካሪ | የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ | ሁለተኛ | 590,000.00 | የካቲት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00-6፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ
- 1. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት አይነት፤ የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ፅ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን እስከ የካቲት 09 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
- 2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ፡ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- 3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካቲት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00-6፡00 በዲስትሪክቱ ፅ/ቤት ይካሄዳል።
- 4. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር የሚታሰብለት ሲሆን ለተሸነፉት ያስያዙት ጎንዘብ ወዲያውኑ ይመለሳል።
- 5. አሸናፊው ያሸነፈበትን ዋጋ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል ንብረቱን መረከብ ሲኖርበት፤ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የጨረታ አሸናፊነቱ ይሰረዛል።
- 6. ገዥው ንብረቱን በገዛበት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% (አስራ አምስት በመቶ) መክፈል ይጠበቅበታል።
- 7. አሸናፊው ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት ከፈለገ የባንኩን ብድር መስፈርት ማሟላትና ቢያንስ 15% ቅድሚያ ክፍያ መክፈል ይኖርበታል
- 8. ስም ማዛወሪያና በሽያጩ ምክንያት የሚፈለግ ማንኛውንም የመንግስት ክፍያዎች በሙሉ ገዢው ይሸፍናል።
- 9. ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር ሁኔታ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የፕሮጀክት ማስታመሚያና ማገገሚያ ቡድን በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 034441-9016 ወይም 034-441 -0233 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
- 10. ንብረቱን መመልከት የሚፈልግ ተጫራች የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለዲስትሪክት ፅ/ቤት በግንባር ቀርቦ መመልከት ይቻላል።
- 11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት
መመለስ