1 የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣
2 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ሰርትፍኬትና የመጨረሻ ወር የቫት ዲክላሬሽን የሚያቀርቡ
3 የዘመኑ የታደሰ የአቅራቢነት የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
4 የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
5 ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
6 ተጫራቾች አሸናፊ ሁነው ሲገኙ ውሉ ከታሰረበት በ60 ተከታታይ ቀናት የኤሌክትሮኒክ እቃዎቹ ማቅረብ የሚችሉ
7 ተጫራቾች 100,000.00 የኢትዮጵያ ብር የጨረታ ማስከበርያ በሲፒኦ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
8 ተጫራቾች የጨረታው ሰነደቻቸውን በሁለት የተለያዩ ኤንቨሎፖች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል ሰነዶች ለያይተው በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።በተጨማሪም ከቴክኒክ እና ከፋይናንሻል ሰነድ አንድ አንድ ኮፒ በማሸግ ፌርማና የድርጅቱ ማሕተም በማሳረፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፣
9 የጨረታው ሰነድ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመክፈል መቐለ በሚገኘው ትግራይ ልማት ማህበር ፅ/ቤት ከቢሮ ቁጥር 430 ወይም አዲስ አበባ ቦሌ መድሃኒ አለም ፊትለፊት 7 ፎቅ የሚገኘው ህድሞና ህንፃ ቢሮ ቁጥር 12 መውሰድ ይችላሉ፣
10 ይህ ጨረታ በማስታወቅያ በወጣ በ16ኛው በ8:30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 9:00 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት በትግራይ ልማት ማሕበር መቐለ በሚገኘው ዋና ፅ/ቤት ይከፈታል፣
11 የጨረታ መክፈቻው ቀን የበአል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፣
12 አሸናፊዎች ያሸነፉት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መቐለ በሚገኘው የትግራይ ልማት ማሕበር ዋና ፅ/ቤት ማድረስ ይጠበቅባቸዋል
13 አሰሪው ፅ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፤-0344406944 መጠየቅ ይቻላል
ድሕሪት