ድርጅታችን መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የመቐለ ባለ ሶስት ኮከብ ሆቴል ፕሮጀክት 11-03B / Massonery Stone/ ስራ ማሰራት ስለሚፈልግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 12/06/2011ዓ/ም ጀምሮ እስከ 16/06/2011ዓ/ም ከጧቱ 4:00 ድረስ የምትወዳደሩበት ሙሉ ሰነድ በጨረታ ሳጥን በማስገባት እንድትወዳደሩ እየጋበዝን ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 16/06/2011 ዓ/ም ከጧቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4:30 ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸውን መመዘኛዎች ከ1-6 ተራ ቁጥር የተገለፁ ነጥቦች ይሆናሉ፤

1 የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና በጠጠር በኣሸዋ እና በድንጋይ የኣቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

2 የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይነት የተመዘገቡበትን ሰርቲፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤

3 የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ 5000.00 ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤

4 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከሌሉ የሚያስገቡት የዋጋ ዶክሜንት ኣይከፈትም ወይም በሌለንበት ይከፈትልን የሚል ፊርማ በማህተም ተደግፎ ሊደረግለት ይግባል፤

5 በሚያስገቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ ካለ ተወዳደሪው ከጨረታው ውጭ ይሆናል፤

6 በሚያስገቡት ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ቨኃላ መሆኑ በግልፅ መቀመጥ ኣለበት፤ይህ ካለሆነ ግን ዋጋው ከነቫቱ እንደሆኑ ይወሳድል፤

7 ፕሮጀክቱ የተሻለ ኣማራጭ ካኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

ኣድራሻ መቀለ ኣክሱም ሆቴል ፊት ለፊት የድሮ ደጀን ሆስፒታል የነበረው ግቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 02 ይሆናል፤

ድሕሪት
ጨረታ መደብ