በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የውሃ ሃብት ቢሮ ለቢሯችን አገልግሎት የሚውሉ የመኪና ስፔርፓርትና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የውሃ ሃብት ቢሮ ለቢሯችን አገልግሎት የሚውሉ የመኪና ስፔርፓርትና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት የሚቀጥለውን መስፈርት የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ።

1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና ብቃት ያለው የንግድ ድርጅት ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ለማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሣ ብር) በመክፈል ከዚህ በታች ከተጠቀሱት አድራሻዎቻችን ማግኘት ይችላሉ።

3. በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የውሃ ሃብት ቢሮ መደበኛ ግዥ ክፍል

4. የጨረታ ሰነዶችን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከታች በተገለጸው አድራሻችን በመቅረብ ማግኘት ይቻላል።

5. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ቫት ዲክለሬሽን፣ የአቅራቢነት መለያ ካርድ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NUMBER) ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

6. ተጫራቾች ለስፔር ፓርት ብር 50,000፣ ለጎማ ብር 10,000 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን «በሁለት ፖስታ» አንድ «ኦሪጅናል» እና ሁለት «ኮፒ» በሰም የታሸጉ ኤንቨሎፖች እስከ 28/1/2011 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በፊት ከላይ በተጠቀሰው የፅ/ቤቱ አድራሻ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት አለባቸው።

8. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን 28/1/2011 ዓ.ም ከቀኑ 9፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፅ/ቤቱ ቢሮ መደበኛ ግዥ ክፍል ይከፈታል። በተጨማሪ ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር፡- 0342413232/0344411795 በተጠቀሰው አድራሻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

9. ይህ ጨረታ የሚቆይበት ጊዜ (Validity period) ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለ60 የስራ ቀናት የፀና ይሆናል።

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የውሃ ሃብት ቢሮ መደበኛ ግዥ ክፍል።

በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የውሃ ሃብት ቢሮ

ድሕሪት
ጨረታ መደብ