1 ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ትግራይ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ቁጥር 23/100 መቶ ብር በመክፈል መዉሰድ ይቻላል
2 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25000 በጥሬ ገንዘብ ወይም ከባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም ስፒኦ ማስያዝ አለባቸዉ
3 ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉ የዘመኑ ግብር የከፈሉና ፈቃደቸዉን ያደሰ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በየወሩ ለግብር ሰብሳቢ ኣካል የከፈሉ መሆናቸዉን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል በተጨማሪም የታደሰ የኣቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
4 የጨረታ ሰነድ በኣማርኛ ቆንቆ የሚሞላ ሆኖ በግልፅ በሚነበብ ሁኔታ የተዘጋጀና ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን ይኖርበታል
5 የጨረታ ሰነዱ ጨረታ ከወጣበት ቀን ከ 5/8/2010 ዓም እስከ 22/8/2010 ዓም በትግራይ ክልል ወጣቶች ስፖርት ቢሮ ቁጥር 23 በሥራ ሰዓት በመገኘት መዉሰድ የሚቻል መሆኑን በተመሳሳይ ግዜ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱ ስም ፊርማ ማህተም በማስፈር ጨረታ ሳጥኑ ዉስጥ ማግባት ይቻላል
6 የጨረታ ሳጥን 22/8/2010 ዓም ሰዓት 9:00 ተዘግቶ 22/8/2010 ዓም 9:30 ሰዓት ይከፈታል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን ተወካዩች ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታዉን ለመክፈት የሚያዳግት ነገር ኣይኖርመ
7 አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ጊዜ በሃላ ባሉት ሶስት ቀናት ዉስጥ ዉል ማሰር ይኖርበታል
8 አሸናፊዎች ተጫራቾች ያሸነፉባቸዉን እቃዎች ዉል ካሰረ በሃላ ባሉት 20 ቀናት ዉስጥ እቃዉ የትግራይ ክልል የወጣቶች ስፖርት ቢሮ መቀሌ ከተማ ባለዉ ጽቤት በራሱ ትራንስፖርት ኣቅርቦ የማስረከብ ግዴታ አለበት
9 ቢሮዉ በሚገዙት እቃዎች ላይ እንደ አስፈላጊነቱ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለዉ
10 ዋጋዉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ባሉት ቀጣይ 60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል
11 ቢሮዉ የተሻላ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ ያለዉ መሆኑን
12 ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0344408877 በመደወል ወይም መቀሌ ከተማ በሚገኘዉ የትግራይ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ቁጥር 23 በኣካል በመገኘት መጠየቅ ይቻላል
ኣድራሻ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ክልል ትግራይ ጉዳዮች ፊት ለፊት ደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ኮምፕሌክስ ህንፃ
ድሕሪት