የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማኀበራዊ ዋስትና አስተዳደር የግዥ አፈጻጸም ሥርዓትን ለመወሰን ባወጣው የግዥ መመሪያ መሰረት በሰሜን ሪጅን የመቀሌ ጽ/ቤት የቢሮ እድሳት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-
ሎት1. የቢሮ አድሳት ስራ፤
ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ (ከሊራንስ) ከገቢዎች ሚኒስቴር የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች, የጨረታውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መቀሌ የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ጽ/ቤት መግዛት የሚችሉ ሲሆን የሚጫረቱበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በሚገኘው የስራ ዝርዝር መሰረት በመሙላት የቴከኒካል እና የፋይናንሽያል ሰነድ በኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መቀሌ የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ጽ/ቤት ማስገባት አለባቸው፡፡
1. ተጫራቾች ለተፈላጊ አቅርቦቶች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ዋስትና በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
2. ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያው በወጣ በ6ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈተውም በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት መቀሌ የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ሪጅን ጽ/ ቤት ነው፡፡ 16ኛው ቀን የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው ሰዓት በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
3. አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 034 241 57 58
ድሕሪት