የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2016
የትግራይ ክልል ግብርናና ተፈጥሮ ኃብት ቢሮ ከዚህ በታች የተጠቀሱት የተለያዩ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ማለትም፦
- ሎት 1 የተመጣጠነ የዶሮዎች ምግብ ግዥ
- ሎት 2. የጓሮ አትክልት ዘር
- ንዑስ ሎት 2.1 የጓሮ አትክልት ዘር ከግብርና ሚኒስተር በተገኘው በጀት
- ንዑስ ሎት 2.2 የጓሮ አትክልት ዘር ከጤና ሚኒስተር በተገኘው በጀት
በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እየጋበዝን፤ የተዘጋጀው የጨረታ ዶክሜንት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ ቅርንጫፍ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000539035658 ገቢ በማድረግ 19/09/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳችሁን በመያዝ ከቢሮአችን የዕቃ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 በሥራ ሰዓት እየመጣችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፣
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ቀጥስው የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የVAT ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና ያለፈው ወር ቫት (Vat) ዲክለር የተደረገበት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መቅረብ አለባቸው፣ ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን ብጥንቃቄ አይተው መወዳደር አለባቸው፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በጨረታ ዶክመንቱ ላይ የተጠቀሰው መጠን ገንዘብ በCPO አሰርተው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ቢሮአችን በጨረታ ከቀረበው የዕቃዎች ብዛት እስከ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው 03/10/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ወድያውኑ 4፡00 መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮአችን የዕቃ ግዥ ክፍል ይከፈታል።
- ቢሮአችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡-034 440 3663/ 034 440 4346 ወይም 034 440 3663 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
ድሕሪት