በከሳሽ ቅዱስ ሚካኤል ራስን ማገዝ ሐበ/መኖርያ ቤቶች ህ/ስ/ማህበር እና
በተከሳሾች 1. ብራዘርስ ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
2 . ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራስ አ/ማህበር ቅርንጫፍ መቐለ መካከል ባለው የአፈፃፀም ክርክር ንብረትነቱ የ 1ኛ ተከሳሽ ብራዘርስ ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሆነ ሊዝ ማሽን ሞዴል OLD ስፐስፌኬሽን Ø800*4M የሚሰራ በጨረታ እንድሸጥ ስለታዘዘ መነሻ ዋጋ ብር 900,000 (ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር ) ሆኖ መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ለ6/9/2016 ዓ/ም ከ 3:00 ሰዓት ጠዋት እስከ 5:00 በመቐለ ከተማ ክ/ከተማ ሰሜን ሰላም ቆርቆሮ ፋብሪካ አጠገብ ስለሚካሄድ በቦታው ላይ በተገለፀው ሰዓትና ቀን ተገኝታቹህ ጨረታው እንድትሳተፉ፤ የጨረታው አሸናፊ 25% ቅድሚያ ማስያዝ ያለበት ሲሆን፡፡ የጨረታ ውጤት በዚያው ቀን 8:00 ሰዓት እንዲቀርብ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመቐለ ያስቻለው ፍታብሄር ችሎት አዟል ።
የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍታብሄር ምድብ ችሎት
ድሕሪት