ትራንስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ የግል ማህበር ባዘጋጀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ኮምፒተሮች፣ ፕሪንተሮች ፣ፋክስ ማሽኖች፣ ላፕ ቶፕ ኮምፒተሮች እና ፎቶ ኮፒ ማሽን በጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል
  1. ተጫራቶች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2008 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸው ያሳደሱ መሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣ (የማስረጃው ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ያስፈልጋል)።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡዋቸው ዕቃዎች በተያያዘው ስፔስፍኬሽን መሰረት መሆን አለበት ፣ ይህ ካልሆነ ከስፔስፍኬሽን ውጭ የቀረበው ዕቃ ከጨረታው ውጭ ይሆናል።
  3. ተጫራቶች የጨረታ ዋጋቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚጨምርና የማይጨምር መሆኑ በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው፣ ካልገለፁ የጨረታ  ዋጋው የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዳካተተ ይቆጠራል።

4.የጨረታው አሸናፊ ጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ  ያሸነፋቸው ዕቃዎች በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ ወይም  መቀሌ በሚገኘው ስቶራችን በራሱ ትራንስፖርት በማጓጓዝ ማስረከብ  አለበት።

5. ተጫራቾች ያሸነፋት ገንዘብ ክፍያ የሚፈፀምላቸው ያሸነፋት ዕቃ ኢንስፔክት ተደርጎ የገቢ ደረሰኝ (GRV) ተቆርጦ መጋዘን እንደገባ  መሆኑ ተጫራቾች አስቀድመው ማወቅ አለባቸው።

6.ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን ከጥር 18/05/2008 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ከመቐለ ግዥና ፣ ንብረት አቅርቦትና ቁጥጥር መምሪያ ቢሮ ወይም አዲስ አበባ ላይዘን ኦፊስ በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላል።

7.የጨረታው ማስረከቢያ ከጠቅላላ ያስገቡት ዋጋ 2% በትራንስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም በሲፒኦ (CPO) መልክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣ CPO ያላስያዘ ተጫራች ወድያው ከጨረታው ይሰረዛል።

8.ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸው ሞልተው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ የካቲት 04/ ቀን 2008 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከጥዋቱ 4፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ የግዢ፣ ንብረት አቅርቦትና ቁጥጥር መምሪያ ቢሮ እና በአዲስ አበባ ላይዘን ኦፊስ ግዢ ማስተባበሪያ ቢሮ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

9.በጨረታ ሰነዱ የተቀመጠ ቁጥርም በPO ጊዜ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

10.ጨረታው በዚሁ ቀን ማለትም የካቲት 10 ቀን 2008 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ፣ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ላይዘን ኦፊስ ግዢ ማስተባበሪያ ቢሮ እና በመቀሌ ዋና መ/ቤት በትንሿ አደራሽ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች በዕለቱ ካልተገኙም የጨረታ ሰነዱ የተሟላ ከሆነ ይከፈታል።

11.ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12.ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 034-441 64 39/034-440 82 05 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

ትራንስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

 

ድሕሪት
ጨረታ መደብ