- ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን : ጥር/9/2012
ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን : ለ10ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10:30 ሰዓት
ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን : በ10ኛዉ ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 11ኛዉ ሰዓት
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሠዓት ሠመራ በሚገኘው በዋና መ/ቤታችን ግዥ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ በ2012 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃዳቸውን፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፊኬት በደረጃ 5 የህንፃ ወይም የጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት የታደሰ ፈቃድ እንዲሁም የመንግስት መ/ቤቶች በሚፈጽሙት ግዥ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አብሮ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 2% ወይም ከ20 ሺህ ብር ያላነሰ ዋጋ ያለው በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን አፋር ገጠር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት ግዥ/ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት ሆኖ ወዲያውኑ ሳጥን ታሽጐ በዚያው ቀን 11ኛው ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:- ሠመራ
ስልክ ቁጥር፡-03366600 79
የመ.ሳ.ቁ 41
ድሕሪት