የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ዓኮስሆ 02/2016
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ዓይደር-ኮምፐርሄንሲቭ እስፔሻላዝድ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: በዚህም መሰረት
1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና ፍቃዱንም በዘመኑ የታደሰ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
2. በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን እና መስፈርት መሰረት ማቅረብ የሚችል፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ምዝገባ ስርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፣
4. የአቅራቢዎች የምስክር ወረቀት ወይም በግዢ ኤጀንሲ ዌብ ሳይት በኣቅራቢነት የተመዘገበና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት/ቲን/ ኮፒ ማቅረብ የሚችል
መለያ | የጨረታው አይነት | የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
ሎት 1 | ኮምፒውተርና ፕሪንተር | 50,000.00 |
በባንክ የተመሰከረለት CPO/ሲፒኦ/ ወይም የባንክ ዋስትና በመቐለ ዩንቨርሲቲ ዓይደር ኮምፐርሄንሲቭ አስፐሻላዝድ ሆስፒታል ስም ማሰያዝ የሚችሉ
5. ማንኛውም ተጫራች ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን የማይመለስ 300 /ሦስት መቶ / ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ ከመቀሌ ዩንቨርስቲ ዓይደር ኮምፐርሄንሲቭ እስፔሻላዝድ ሆስፒታል ግቢ በግዥ ንብረት እና ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላል፣
6. ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
7. ጨረታው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ጥዋት 3፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ልክ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል። 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣
8. በጨረታው አሸንፎ በወቅቱ ውል ለማያስር የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ CPO ኣይመለስለትም፣
መቐለ ዩንቨርሲቲ ዓይደር ኮምፐርሄንሲቭ እስፐሻላዝድ ሆስፒታል የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ፡- ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ዓይደር ኮምፐርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ በግዥ ንብረት እና ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላል፣ ስ.ቁ 0344416672/90 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ዓይደር ኮምፒርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ
ሆስፒታል ግዢ፣ ንብረት እና ፋይናንስ ቡድን
መመለስ