- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና ፍቃዱም በዘመኑ የታደሰ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርቲፍኬት ማቅረብ የሚችል ወይም በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብሳይት የተመዘገበ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገበና የምዝገባ ሰርቲፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል። ለጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ)
- ለፈርኒቸር ዕቃዎች ------ ብር 60,000.00 ሎት አንድ
- ለኤሌክትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፡- ብር 40,000.00 ሎት ሁለት
- ለፅሕፈት መሳሪያ ዕቃዎች -------- ብር 50,000.00 ሎት ሦስት በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ የሚችል።
- በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችል።
- ማንኛውም ተጫራቾች ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራቾች ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የኢተዮጵያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት - መቐለ ዋና ግቢ ቢሮ ቁጥር 219 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀንና ወር ጀምሮ በ22ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል። በ 22ኛው ቀን በዓል ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ጨረታውን አሸንፎ በወቅቱ ውል ለማያስር የጨረታ አሸናፊ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ቢድ ቦንድ አይመለስለትም። ኢንስቲትዩቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 034 441 2807 /034 441 9039 ደውሎ ማነጋገር የሚቻል መሆኑ በማሳሰብ ጭምር ነው።
የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
ድሕሪት