ደደቢት ትካል ልቓሕን ምዕቒርን አ/ማ
DEDEBIT CREDIT & SAVING INSTITUTION S/C
የጨረታ ማስታወቂያ
ደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም አ/ማ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለሆነም የ2011 ዓ.ም የመንግስት ግብር የከፈላችሁበት እና ቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁ የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ማስከበርያ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ CPO ለድርጅቱ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል
- የጨረታ ማስከበርያ ከጠቅላላ ዋጋ ከ2% በታች ያስያዘ ከጨረታ ይሰረዛል
- ተጫራቾች የጨረታ ደኩሜንት መቐለ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 እንዲሁም አዲስ ኣበባ በሚገኘው ተክለሃይማኖት ቅርንጫፍ ብር 100 በመክፈል ከ28/8/2011 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ሰአት መውሰድ ይቻላል
- በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በታሸገ ኢንቨሎፕ መቐለ ዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 09/9/2011 ዓ.ም ከቀኑ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ትችላላችሁ
- ተጫራቾች ወይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ09/9/2011 ዓ.ም ከቀኑ 3:30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል ተጫራቾች ወይ ህጋዊ ወኪል ባይገኙም የተሟላ ደኩሜንት ካለ ጨረታው በተገለፀው ሰአት ይከፈታል
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታው ውጤት እንደተገለፀ ከጠቅላላ ዋጋ 10% የሥራ አፈፃፀም ማስከበርያ /peromance bond/ ማስያዝ ይኖርበታል
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት እንደተገለፀ በ5 ቀን ውስጥ ውል ማሰር ይኖርበታል
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ስበስበ መረጃ መቐስ በሚገኘው ዋና ቢሮ 35 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 11 ወይም በስልክ ቁጥር 0342-40-00-14 በመደወል ማረጋገጥ ይቻላል፡
ደደቢት ብድርና ቁጠባ አ/ማ
መመለስ