በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ዕዝ ጠመምሪያ ለ 2011 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚዉሉ ከዚህ በታች የተገለፁትን በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ማስጠገን እና የሰርቪስ አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል

ሎት 1 የተለያዮ የኮንስትርክሽን ዕቃዎች እና ብረታ ብረቶች ሎት 2 የተለያዮ የኤለክትሪክ ዕዋዎች ሎት 3 የተለያዮ የባንባ ዕቃዎች ሎት 4 የተሸከርካሪ ጎማ ካላማደሪያ ፍላጥ እና ባትሪ ሎት 5 የማሽነሪ እና የጀነሬተር መለዋወጫ ዕቃዎች ሎት 6 የኤለክትሮነስ እና የኦፊስ ማሸን መለዋወጫ ዕቃዎች ሎት 7 ቃሚ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸር) ሎት 8 አሸዋ ጠጠር እና ድንጋይ ሎት 9 የተለያዮ መጠን ያላቸዉ አጠናዎች ሎት 10 የብሎኬት ምርት ማምረት ሎት 11 የግሬደር ጥገና ሎት 12 ሴራሚክ የመሬት ወለል ማንጠፍ ሎት 13 የመኪና ሰርቪስ ኪራይ

በዚህም መሠረት ከሎት 1 እስከ ሎት 12 ለተጠቀሱት በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፣ የቫት ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸውን እንዲሁም ሎት 13 ለመኪና ሰርቪስ ኪራይ በስራው የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ለሚያቀርቧቸው ሰርቪስ መኪናዎች ሙሉ ኢንሹራንስ የተገባላቸውና ስለመኪናቸው ከመንገድ ትራንስፖርት እውቅና ያገኙ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ይጋብዛል። 

ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ እና ዝርዝር ሰነድ የያዘ ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ለእያንዳንዳቸው ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሣ ብር) እና ከሎት 8 እስከ ሎት 13 ለእያንዳንዳቸው ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መቀሌ ኩሓ መንገድ እግረ ወንበር አካባቢ ከሚገኘው የጠቅላይ መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመግዛት በቢሮው ወደ ተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 

መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0344 41 07 50

ድሕሪት
ጨረታ መደብ