ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት የኮምፒውተርና ኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ፤
- የጨረታ ስፔስፊኬሽን/ዝርዝር መግለጫ/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መግዥያ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው በመምጣት መግዛትና ሰነድ ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ሃምሳ ሺህ /50,000/ ብር በC.P.O ከህጋዊ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የእቃውን ዝርዝር ነጠላ እና ከቫት ጋር ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ አድርገው በተሰጠው ስፔስፊኬሽኑ መሰረት በመሙላት ፋይናሻል ኦርጂናል ቴክኒካል ኦረጂናል ፋይናንሻል ኮፒ ቴክኒካል ኮፒ ለብቻ በፖስታ ከታሸገ በኋላ በመጨረሻ ሁሉንም በኣንድ ፖስታ ታሸጎ በግ/ፋ/ን/ኣስ/ቡድን ማቅረብ ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ከቀኑ 7:45 ታሽጎ 8:00 ላይ ይከፈታል። የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 8:00 ላይ ይከፈታል።
- የቀረበው የዋጋ መወዳደሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ ለ30 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋ/ን/ኣስ/ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 10 38 50 45/09 33 48 71 40/09 14 03 45 39
አድራሻ ዓዲሽምድሖን ዳሽን ባንክ ፊት ለፊት
በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት
ድሕሪት