- ቁጥር አፋር -01/2013
- ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን በጋዜጣ የወጣበት ቀን: 14/1/2013
ጨረታ የሚዘጋበት ቀን በ11ኛዉ ቀን :ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን በ11ኛዉ ቀን: ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- የኮምፒዩተር አክሰሰሪዎችን እና
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታአወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
- ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ስራ ፈቃድ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት
- በመንግሥት አቅራቢነት የተመዘገበ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ያለው
- ተጫራቾች በየሎቱ/በሚወዳደሩበት ዕቃዎች 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ይመለስላቸዋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያበአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሲቪል ሰርቪስና አቅም ግንባታ ቢሮ የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 32 የማይመለስ ብር 50.00 ( ሃምሳ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም የጨረታ ተወዳዳሪ በሚያቀርበው የዕቃዎች ዋጋ በግልጽና በማያሻማ መልኩ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ከዚህ መመሪያጋር በተያያዘ ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ የነጠላ እና የጠቅላላ ዋጋውን ከነቫቱ ሞልቶ ከላይ የተጠቀሱትና ማስረጃዎች አሟልቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ሠመራ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሲቪል ሰርቪስና አቅም ግንባታ ቢሮ ምድር ላይ በሚገኘው የመረጃ ዴስክ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ እና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የሚዘጋ ሆኖ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምክንያት በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ሲቀር የጨረታውን መክፈት እያስተጓጉልም።
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በቢሮው ስልክ ቁጥር፡- 033-666-01-36/0137 ወይም በፋክስ ቁጥር 033-666-04-08/06-39 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት
ልማት ቢሮ
ሠመራ
ድሕሪት