ተሽከርካሪዎቹ የሚሠሩበት ቦታ በጨረታ ሰነዳችን በዝርዝር ተቀምጠዋል።

ተ.ቁ.

የተሽከርካሪው ዓይነት

የሚፈለገው የተሽከርካሪ ብዛት

የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የመክፈቻ ቀንእና ሰዓት

1

አይሱዙ 35 ኩንታል የሚጭን

18

ሐምሌ 11 ቀን2011 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት

ሐምሌ 11 ቀን2011 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት

2

ሲንግል ጋቢና

8

3

ደብል ጋቢና ፒክ አፕ

9

  1. በጨረታው መስፈርቱን የሚያሟሉ በዘርፍ የተሰማሩ ብቃት ያላቸው የንግድ ድርጅቶች ወይም የተሽከርካሪ ባለንብረቶች መወዳደር ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ያከናወኑበትን እና የተሽከርካሪዎቹን 3ኛ ወገን የኢንሹራንስ ዋስትና ማስረጃ የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ድርጅቱ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከዚህ በታች ከተጠቀሰው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ማግኘት ይቻላል፤

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መቐለ ዲስትሪክት /ቤት

በዲስትሪቡሽን ኮንስትራክሽን ኦፕሬሽንና ሜንቴናንስ ቢሮ ቁጥር 15

ፖስታ ሳጥን ቁጥር -472

ፋክስ ቁጥር፡- 0344-40-6477 የስልክ ቁጥር፡- 0344409568

መቀሌ-ትግራይ-ኢትዮጵያ 03 ቀበሌ ኣግኣዚ ህንፃ አጠገብ

መቀሌ

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለጨረታው እንደሚያቀርቡት ተሽከርካሪ ብዛት ማለትም 1/አንድ/ ተሽከርካሪ የሚያቀርቡ ከሆነ 5,000.00 /አምስት ብር /2/ ሁለት ተሽከርካሪዎችን የሚያቀርቡ ከሆነ 10,000.00 /አስር ብር /3/ ሶስት ተሽከርካሪዎችን የሚያቀርቡ ከሆነ 15,000.00 /አስራ አምስት ብር/ እያለ በሚወዳደሩባቸው መኪና ብዛት ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በመሥሪያ ቤታችን ስም ሲፒኦ /CPO/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ማሠራት አለባቸው።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ዲ/ኮ/ኦ/ሜ-001/2012 ዓ.ም- የሚል ምልክት በማድረግ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናልና ኮፒ በመፃፍ እስከ ከቀኑ 800 ሰዓት በፊት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመቐለ ዲስትሪክት ፅ/ቤት 2ኛው ፎቅ ያለ አዳራሽ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ 830 ሰዓት ይከፈታል

7.ዲስትሪክቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡