1 የዘመኑ ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የቅርብ ወር 2012 ዓም ቫት ሪፖርት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2 የጨረታ ማስከበሪያ ለዶዘርና ግሬደር ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒአ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በፅህፈት ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3 ተጫራቾች ሰነድ ጨረታ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል ሰነድ ጨረታ መውሰድ ይችላሉ፡፡
4 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለእያንዳንዱ አንድ ኦርጅናል ከሁለት ኮፒ ለየብቻው ጠቅላላ 6 የታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5 ጨረታው ቀን 25/09/2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6 ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ገፅ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
7 ፅህፈት ቤታችን ጨረታ ከተከፈተ በኋላ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
8 ፅ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0345593411/ 0342408757 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡