1 በዘርፍ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ማለት የ2011 ዓ/ም ግብር የከፈሉና ያሳደሱ የመንግስት ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2 በክልል ፕላንና ፋይናንስ ቢሮ ወይም በፌደራል መንግስት ግዚ ኤጀንሲ ያአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸው ማረጋገጫ የሚያቀርቡትና መለያ ቁጥር ያላቸው።
3 ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ከፋይ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤
4 ኢምፖርትና ኤክስፖርት የሚያደርጉ ከሆኑ የተሰጣቸው የኣስመጪና ላኪ ማረጋገጫ የሚያቀርቡ፤
5 ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያው ቢድ ቦንድ ብር 50000.00 (ኣምሳ ሺ)፤ በጥሬ ገንዘብ ወይም ብባንኪ የተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ፤
5 ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለሚጫረቱበት ዓይነት የማይመለስ ብር 100.00 ( ኣንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በኣዲስ ዘመን ቀን ጀምሮ ከ18/03/2011 ዓ/ም 17/04/2011 30 ለተከታተይ ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግዥ/ ፋይ /ንብረት ቁጥር 23 በመምጣትና በመወስድና በ30 ቀናት ውስጥ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ፖ.ሳ.ቁጥር 328 በኣድራሻ በመላክ ወይም በግንባር በመቅረብ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በስራ ሰኣት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላል።
6 ጨረታዉ በቀን 18/04/2011 ዓ/ም ጥዋት 4:30 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዕለቱ 5:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የተሻለ ቢሆንም፣ ባይገኙም ግን በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በግዚ ክፍል ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻው ቀን ህዝባዊ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ይከፈታል።
8 የጨረታ ኣሸነፊዎች ላሸነፉት እቃ ውል የማሰር ( የመግባት) ግዴታ ኣለባቸው። በገቡበት ውል መሰረትም ይፈፅማሉ፤ በገቡት ውል ሳይፈፅሙ ቢቀሩ ብእያንዳንዱ ቀን ካስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 0.1% ቅጣት ገቢ ይደርጋሉ። ወይም በህግ ይጠየቃሉ።
9 ለቢሮ እቃ በቀረበው የጨረታ ሰነድ የእያንዳንዱ ዓይነትና ብዛት የተገለፀው ቁጥር በ20% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።
10 ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት መሆኑ ማወቅ ይኖርባቸዋል።ይህ ቴክኒክና የፋይነንሻል ግምገማዎች ተጠናቅቀው ኣሻነፊው እሰከ መለየትና ማሳወቅ እንዲሁም የቅሬታ ግዜ ተጠቅልሎ ካሸናፊው ጋር ውል እስኪታሰር የሚወስደው ግዜ ማለት ነው።
11 ተጫራቾች በቀረበው ጨረታ ሰነድ ኣስተያየት ካላቸው ከጨረታ መክፈቻው ሰዓት በፊት ማቅረብ ይችላሉ። በጨረታው መክፈቻ ግዜ ከሆነ ግን ተቀባይነት ኣይኖረውም።
12 መስሪያ ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዘ መበቱ የተጠበቀ ነዉ::
13 በስቶክ/መጋዚን/ ቅድሚያ ያለው ይመርጣል።
ቢሮዉ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0344-402420 /0344-411201 መጠየቅ ይችላሉ::
Backs