ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በሰሜን ሪጅን የእ/ስላሴ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታማሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።
- ከ 18 እስከ 20 ክፍል ወይም እስከ 250 ሜ.ካሬ ሆኖ ለቢሮ አቀማመጥ እና ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ የሆነ/በተለይ ለአረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች እንዲሁም የእያንዳንዱ ክፍል ስፋት 3*4m2 እና ከዚያ በላይ የሆነና ከ G+1 ያልበለጠ
- ውሃና መብራት፣ ሻወርና መፀዳጃ ቤት ያለው/የሚሰራ/ ሲሆን የሚቀጥለውን መስፈርት የምታሟሉ የቤት ባለቤቶች መወዳደር ትችላላችሁ።
- በሽረ ከተማ ውስጥ ለጡረተኛ ማህበረሰብ ማእከል እና ከመነሃርያ አቅራቢያ ፊት ለፊት የሆነ እስከ ገባር ሽረ ሆቴል ፊት ለፊት መስመር ቀበሌ 02 እና ቀበሌ 05 ከዋናው አስፋልት 3 መንደር ገባ ያለ መሆን አለበት።
- ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢዎች ከሆኑ የማስረጃውን ኮፒ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሚሰጡትም ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባቸው ፤ ካልተገለፀ ከነ ቫት እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ደረሰኝ እና የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ድረስ ሰሜን ሪጅን በእ/ስላሴ ቅ/ፅ/ቤት ቀርበው በመግዛት የሚያከራዩበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡- በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በሰሜን ሪጅን የእ/ስላሴ ቅ/ፅ/ቤት ሽረ
የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
በሰሜን ሪጅን የእ/ስላሴ ቅ/ፅ/ቤት
Backs