የትግራይ ክልል ጊዝያዊ ኣስተዳደር ጤና ቢሮ ከታች በሎት የተጠቀሱ እቃዎች ከህጋውያን ነጋዲዎች በጨረታ ኣወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለዚህ መስፍርቱን የምታሟሉ ህጋውያን ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

+ ሎት-1 የኮምፒዩተር እና ተዛማጅ እቃዎች

+ ሎት- የኦፊስ ፈርኒቸር እቃዎች

መሟላት ያለባቸው መስፍርቶች

1. የ2016 የታደሰ ንግድ ፍቓድ ፣ የግብር ከፋይ ፐ ምዝገባ ሰርትፍኬት እና የታደሰ የኣቅራቢዎች ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ ኣለባቸው።

2. የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቐት እና የ2016 ዓ.ም ያለፈው ሰዎስት ወር ቫት ዲክሌር ያረጉበት ማሰረጃ ማቅረብ ኣለባቸ

3. የጨረታ ዋስትና ለሎት-1 ብር 50,000 እና ለሎት2 ብር 20,000 በጥሬ ገንዘብ ፣ የተረጋገጠ ቼክ ፣ የክፍያ ትእዛዝ .../ ወይም በሁኔታ ያልተመሰረተ ባንክ ዋስትና ማስያዝ ኣለባቸው።

4. ተወዳዳሪዎች ለሎት-1 የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክሚንት ኦርጅናልና ኮፒ እና ለሎት-2

ፋይናንሻል ዶክሚንት ብቻ ኦርጅናልና ኮፒ ተብለው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰኣት የግዢ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 42 ማስገባት ኣለባቸው።

5. ጨረታው በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ 85ኛ እትም ቁጥር 170 የታወጀ ሲሆን ከ 21 የካቲት 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 05 መጋቢት 2016 ዓ.ም የሚቆይ ሁኖ የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት እንዲሁም ሌሎች ኣስፈላጊ የሆኑ መምርያዎች በሙሉ በሚሸጠው ጨረታ ሰነድ መመልከት ይቻላል።

7. ተዋዳዳሪዎች የሚያስገቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆን ኣለበት ካልሆነ ቫት እንዳካተተ ይቆጠራል።

6. ተወዳዳሪ ኣሸናፊ ሁነው ከተገኙ ለሁለቱም ሎቶች ውል ከገቡት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

8. የጨረታ ሰነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 100.00 /ኣንድ መቶ ብር ከፍለው ከትግራይ ክልል ጊዝያዊ ኣስተዳደር ጤና ቢሮ የግዥ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በስራ ሰኣት መግዛት ይችላሉ።

9. ቢሮው የተሻለ ኣማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው እንድሁም 20% መጨመር ኣልያም መቀነስ ይችላል።

10. ማነኛውም ግልፅ ያልሆነ ጥያቄ ካላችሁ ጨረታ ሰነድ የሚከፈትበት ቀን ከመድረሱ ከ5 ቀናት በፊት በፅሁፍ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

11. ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት BD VALDITY DATE 60 ቀናት ይሆናል።

12. በእያንዳንዱ ንብረት ኣሸናፊ ይለያል በምድር ወይም በጠቕላላ ኣሸናፊ ኣይደረግም።

ለበለጠ መረጃ የትግራይ ክልል ጊዝያዊ ኣስተዳደር ጤና ቢሮ ስ.ቁ 03-44-40-47-15 ደውለው

Backs
Tender Category