በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ዕዝ ጠመምሪያ ለ2012 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እና የሙዚቃ መሣሪያዎች፣ የብር ማስቀመጫ ካዝና እና ሳምሶናይት፣ሰመር ሰብል ፓምፕ እና ኮንትሮል ፓነል ቦርድ፣ የኮንስትራክሽን እና የቧንቧ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ አሸዋ፣ ጠጠር፣ ድንጋይ እና ብሎኬት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና እንዲሁም ለ2013 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የጥሬ ስንዴ አወዳድሮ ማስፈጨት ይፈልጋል
  • ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ እና የሙዚቃ መሣሪያዎች፣ 
  • ሎት 2. የብር ማስቀመጫ ካዝና እና ሳምሶናይት፣ 
  • ሎት 3 ሰመር ሰብል ፓምፕ እና ኮንትሮል ፓነል ቦርድ፣ 
  • ሎት 4. የኮንስትራክሽን እና የቧንቧ ዕቃዎች፣ 
  • ሎት5. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ 
  • ሎት 6. አሸዋ፣ ጠጠር፣ ድንጋይ እና ብሎኬት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና እንዲሁም 
  • ሎት7. ለ2013 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የጥሬ ስንዴ አወዳድሮ ማስፈጨት ይፈልጋል። 

በዚህም መሠረት ከሎት እስከ ሎት6 ለተጠቀሱት በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት፣ የቫት ሰርተፍኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውን ይጋብዛል፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ እና ዝርዝር ሰነድ የያዘ ለሎት1 ፣ ሎት 2 ፣ ሎት 3: ሎት 4 እና ሎት 5 ለእያንዳንዳቸው 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለሎት 6 እና ለሎት 7 ለእያንዳንዳቸው 50 (ሃምሳ ) ብር በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መቐለ ኩሓ መንገድ እግሪ ወንበር አካባቢ ከሚገኘው የሰ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የጨረታ ሰነድ በመግዛት በቢሮው ወደ ተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው ሚያዝያ 13/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: 

  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
  • ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 0344 410750 

በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን 

ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ 

Backs
Tender Category