በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2012 የበጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ማለትም ዊልቸር፣ የፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒከስ ግዥ ለመፈጸም በመስኩ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል
  • ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን  : 14/4/2012
    ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን : በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት  
    ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን :  በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት  
  • ዊልቸር፣
  • የፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒከስ ግዥ ለመፈጸም በመስኩ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም ፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ 
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣ 
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ 
  4. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርብ 
  5. በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ በኤጀንሲው ድረ ገጽ በአቅራቢነትየተመዘገቡበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ 
  6. ተጫራቶች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር / በመክፈል በአፋር ብ/ክ/መንግስት ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ 
  7. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣ ትም 
  8. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ዝርዝር መግለጫ ወይም አስፈላጊውን መረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  9. የጨረታው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 05 በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ተግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል በኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡ 
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% (አንድ ከመቶ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ( ሲፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፣ 
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በ1 /አንድ/ ኦርጅናልና በሁለት ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ 
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ ተጠበቀ ነው፣ 
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አፋር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 666 0162 /0196 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ 

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 

የሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ 

መመለስ
የጨረታ ምድብ