አክሱም ዩኒቨርሲቲ የምግብ ጥሬ እቃዎች እና አትክልቶች፣ የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ ደምብ ልብስ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የወረቀት ህትመት ውጤቶች፣ የቧንቧና የህንፃ መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የመኪና እና የወፍጮ መለዋወጫ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል

 

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ የተገለጹትን እቃዎች

1.የእቃዎች አቅርቦት ግዥ፦

ተ.ቁ የጨረታ ሰነድ ቁጥር/ሎት/ የጨረታ አይነት የጨረታ መሸጫ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ
01 ሎት 01 የምግብ ጥሬ እቃዎች እና አትክልቶች 100.00 100,000.00
02 ሎት 02 የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች 100.00 60,000.00
03 ሎት 03 ደምብ ልብስ 100.00 30,000.00
04 ሎት 04 አነስተኛና ቋሚ የቢሮ እቃዎች 100.00 15,000.00
05 ሎት 05 የጽዳት እቃዎች 100.00 25,000.00
06 ሎት 06 የተለያዩ የወረቀት ህትመት ውጤቶች 100.00 5,000.00
07 ሎት 07 የቧንቧና የህንፃ መሳሪያዎች 100.00 26,000.00
08 ሎት 08 የኤሌክትሪክ እቃዎች 100.00 100,000.00
09 ሎት 09 የመኪና እና የወፍጮ መለዋወጫ እቃዎች 100.00 30,000.00

ከህጋዊ ነጋዴዎች /ስራ ተቋራጮች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ፦

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀንና ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለእቃዎች፣ በዩኒቨርሲቲው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከግዥ ክፍል፣ ህንፃ ቁጥር 53፣ቢሮ ቁጥር 002፣ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች በሥራው መስክ የተሰማሩና ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን የሚያስረዳና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስፈልግ ማስረጃዎች ማያያዝ አለባቸው።

3. የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና በክልል/ፌዴራል/ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

4. ለጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት 3% ልዩ አስተያየት ይደረጋል፡፡

5. ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ15 ቀናት በኋላ ባለው ቀጣይ የሥራ ቀን ሆኖ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በግልጽ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ በመቅረታቸው ጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም፡፡

7. የጨረታው አሸናፊ በጊዜው ቀርቦ ውል የማያስር ከሆነ በጨረታ ሰነዱ የተገለፀው ለጨረታ ማስክበሪያነት ያስያዘው ሲፒኦ /ቢድ ቦንድ/ አይመለስለትም፡፡

8. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 0914-19-18-46/0914189115 ደውለው ይጠይቁ፡፡

መመለስ
የጨረታ ምድብ