የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣98/90 እና 216/92 መሠረት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከተውን ምርት በግልዕ ሐራጅ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የተበዳሪው ሰጪው ስም | የሚሸጠው ንብረት አይነት | ሐራጅ የሚከናወንበት ቦታ | የሐራጁ ደረጃ | የሐራጁ የአንድ ኩንታል መነሻ ዋጋ /በብር/ | ሐራጁ የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት |
አቶ ዮሃንስ ግርማይ | 3581 ኩንታል ማሽላ | በሑመራ ከተማ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኝ የእህል መጋዘን | አንደኛ | 1,346.87 | 04/01/2013 ዓም ከ4፡00-6፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ
- 1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ ¼ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
- 2. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- 3. አሸናፊው ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል መረከብ ይኖርበታል፤ በተጠቀሰው ቀን ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የሐራጁ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ምርቱ ለሁለተኛ ጊዜ ሐራጅ በመውጣቱ ለሚፈጠረው ልዩነት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
- 4. ሐራጁ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የሚመለከታቸው የመንግስት መ/ቤቶች ተወካዮች በተገኙበት በሑመራ ከተማ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኝ የእህል መጋዘን በግልፅ ይካሄዳል፡፡
- 5. ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ወይም በሑመራ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ በስልክ ቁጥር 03-44-419016፣ 0344-410233 ወይም 0342480060 ደውሎ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
- 6. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት
መመለስ