በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት በ 2012 በጀት ዓመት ለቅ/ጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ ግዥ አወዳድሮ ቋሚና አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ የፅህፈት መሣሪያዎችና የፅዳት ዕቃዎች የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችና ጎማዎች፣ የኤሌክትሪክና የሕንፃ መሣሪያ ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
  • ቋሚና አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣
  • የፅህፈት መሣሪያዎችና የፅዳት ዕቃዎች የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችና ጎማዎች፣
  • የኤሌክትሪክና የሕንፃ መሣሪያ ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ዕቃዎችን የሚያመለክተው የጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ መመልከት ትችላላችሁ፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ 

1 ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤ 

2. የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ 

3 ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ 

4 ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ 

5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00(አስር ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤ 

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ሲኤሚሲ/ሚካኤል አካባቢ ከሚገኘው የጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት የግዥ ቡድን ሕንፃ አራተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ መግዛት ይችላል፤ 

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ 

8. ጨረታው የካቲት 5/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ 

9. የጨረታው አሸናፊ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ) CP0 በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፤ 

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ 

ስልክ ቁጥር፡- 022-224-02-47/022-224-16-88 

የጉምሩክ ኮሚሽን አዋሽ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

መመለስ
የጨረታ ምድብ