በሑመራ ከተማ ኮንስትራክሽን መንገድ ትራንስፖርት ፅሕፈት ቤት፤ የፕሮጀክቱ ባለቤት የሆነ የሑመራ ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት በሰቲት ሑመራ ከተማ ቀበሌ 03 ፓኬጅ Humera/CW/BC/01/12 /5th & Final Phase/ 5ኛና የመጨረሻ ምዕራፍ የስታድየም ሥራ ፕሮጀክት በBC-5/GC-6ና ከዚያ በላይ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጭ ፍቃድ ላላቸው ኮንትራክተሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
  • የተለቀቀበት ቀን: ቀዳም ጥሪ 9, 2012 (ከ 5 ዓመታት)
  • መዝግያ ቀን: ሶኒ የካቲት 2, 2012 09:00 ከሰአት (ተዘጋ)
  • የጨረታ ማስከበርያ ዋጋ:450000.00
  • ቦታ: ሐመራ
  • የጨረታ ደኩመንት ዋጋ:500.00
  • ጨረታ ሚከፈትበት ቀንና ሰዓት: ሶኒ የካቲት 2, 2012 09:30 ከሰአት
  • ገዛውቲን ሕንፃ ስራሕቲን/
  • Print
  • Pdf

-የ2012 ዓም የታደሰ የሥራ ተኮናታሪነት ምዝገባ ካርድ፤የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ፤የአቅራቢነት ምዝገባ ካርድ ሰርቲፊኬት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤የወቅቱ ወይም ያለፈውን ወር ቫት ዲክላሬሽን እና የቲን ምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚያቀርብ፡፡ 

  1. የጨረታው ዋስትና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እውቅናና ፍቃድ የተሰጣቸው ባንኮች በሁኔታ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፤የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 450,000.00 (አራት መቶ ሃምሳ ሺ/ ማቅረብ ኣለባቸው፡፡ 
  2. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ፕሮጀክት ሳይት ከተረከቡበት ቀን ጀምሮ በ690 /ስድስት መቶ ዘጠና ተከታታይ ቀናት ሙሉ በሙሉ ጨርሶ ማስረከብ አለበት፡፡ 
  3. ሁሉም ተጫራቾች በሑመራ ከተማ ኮንስትራክሽን መንገድ ትራንስፖርት ፅሕፈት ቤት ሕንፃ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን የሥራ ሂደት የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ከ29/04/2012 ዓ.ም ጀምሮ ከሑመራ ከተማ ኮንስትራክሽን መንገድ ትራንስፖርት ፅሕፈት ቤት ሕንፃ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ። 
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ፕሮጀክት ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻው ዶክመንት አንድ ኦሪጂናል ሰነድ ፣ሁለት ፎቶ ኮፒ የጨረታ ሰነዶች ለሥራ ተኮናታሪነት የተሰጠው ምዝገባ ካርድ፣የሥራ ንግድ ፍቃድ፣የአቅራቢነት ምዝገባ ካርድ ሰርቲፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቫት ዲክለሬሽን ፣ የቲን ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የጨረታው ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ፣ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ መልሶ በሌላ ትልቅ ፖስታ አንድ ላይ በማሽግ ፤ በፖስታው ጀርባ ላይ ለሚጫረቱት ፕሮጀክት ስምና አድራሻ በሚታይ ቀለም በመጻፍ በቢሮ ቁጥር 03 ለጨረታው ተብሎ የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 02/06/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 በአካል በመቅረብ ማስገባት ይችላሉ:: 
  5. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ የቀረቡ መስፈርቶችን በትክክል ሞልተው በያንዳንዱ የጨረታው ሰነድ ገፅ ፊርማቸውና ማህተማቸውን በማሳረፍ ፤ የጨረታው ሰነድ ቅደም ተከተል ሳይዛባ የጨረታ ሰነዱን ልክ ሲሽጥ እንደነበረው ሳያጓድሉና ሳይቀንሱ ማቅረብ አለባቸው።
  6. ጨረታው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 02/06/2012 ዓም ልክ ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ልክ ከጠዋቱ 3:30 በቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል። 
  7. ፅሕፈት ቤቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
  8. ለተጨማሪ መረጃ ሑመራ ከተማ ኮንስትራክሽን መንገድ ትራንስፖርት ፅሕፈት ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በአካል ወይም በስልክ ቁጥር፡- +251-344-48-80/+251-344-48- 18-80 በመደወል ማግኘት ይችላሉ። 

የሑመራ ኮንስትራክሽንና መንገድ 

ትራንስፖርት ፅሕፈት ቤት 

ሕንፃ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን የሥራ ሂደት 

ሑመራ

መመለስ
የጨረታ ምድብ