የአፋር መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኤሮሊ-ኦብኖ ገጠር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ ላይ የሚሰማሩ ማሽኖችን እና ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን ጥቅምት 28/2012    ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን 10 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀነ 11:00    ጨረታዉ የመከፈትበት ቀን 11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:00                                                                                                                                                                                 

ተቁ

የማሽን ተሽከርካሪ አይነት

ብዛት 

1

D8H ዶዘር 

1

2

ኤክስካቫተር 

ከነጃክሃመር 

1

3

ሎደር ማሽን ባለ 3.5 

ሜ.ኩብ 

1

4

ግሬደር ማሽን 280 hp 

1

5

ሮለር ኮምፓክተር ማሽን 

1

6

ገልባጭ መኪና ባለ 

18m3 

5

7

የነዳጅ ቦቲ 17000 በላይ 

1

8

የውሃ ቦቲ 14000 

1

9

መለስተኛ የጭነት መኪና በአይሱዙ/ 

1

10

ሰርቪስ መኪና 

1

በዚህም መሰረት : 

  • ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሠዓት ሠመራ በሚገኘው በዋና መ/ቤታችን ግዥ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
  • ማንኛውም ተጫራች ለሚያቀርባቸው ማሽን/ ተሽከርካሪዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ወይም ሊብሬ ኦርጅናሉን ይዞ በመቅረብ ጨረታውን መወዳደር ይችላሉ፣
  • ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃዳቸውን፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፊኬት እና የመንግስት መ/ ቤቶች በሚፈጽሙት ግዥ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አብሮ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪቢያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 10,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፣
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉትjዕ ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን አፋር መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ግዥ/ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  • ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ለ10 ተከታታይ ቀናት እስከቀኑ 11፡00 ሠዓት ሆኖ ወዲያውኑ ሳጥኑ ታሽጐ በሚቀጥለው 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ 
  • ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

አድራሻ ሰመራ ስልክ ቁጥር፡-033-666-00-79 

የአፋር መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ 

ድሕሪት
ጨረታ መደብ