- ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን በጋዜጣ የወጣበት ቀን : 27/1/2012
ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን : በ 30ኛዉ ቀን 4:00 ሰዓት
ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን : በ 30ኛዉ ቀን 4:30 ሰዓት
- የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድና የአቅራቢዎች መታወቂያ ፍቃድ ያላቸው
- ቫት የተመዘገበና የመጨረሻ ወር ቫት ዲክለር ያደረገ ቲን ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታው ዶክሜንት የማይመለስ 200(ሁለት መቶ) በመክፈል መቐለ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታው ዶክመንት ከደጋፊ ስራ ሂደት ግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ
- ጨረታ ዶክመንቱ ማስገባት የሚቻለው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ወደ ጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ሁሉም ተጫራቾች 50,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በCPO፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የቀረበ ዋስትና፣ ጥሬ ገንዘብ፣ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትእዛዝ፣ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቹ ነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪም በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው መቅረብ አለባቸው።
- በዶክመንቱ ከተሰጠው እስፔስፊኬሽን ውጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ዋጋ በCPO፣ በተረጋገጠ የባንክ ጋራንቲ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የውል ማስከበሪያ (Performance bond guarantee) 10% ማስያዝ የሚችልና በ3 ቀን ውስጥ ውል አስሮ በዶክመንቱ በተጠቀሰው ቀን ንብረቱን ማስገባት የሚችል
- በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግስት ግዢ እንዳይሳተፍ ለማድረግ ወደ ክልሉ ፋይናንስና ፕላን ቢሮ ደብዳቤ እንጽፋለን፡፡
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣው የጨረታ ዶክመንት ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተ ለ60 ተከታታይ ቀናት ብቻ ነው።
- ጽቤቱ ጨረታው እንደ አስፈላጊነቱ ከያንዳንዱ ነጠላ ዋጋ በ20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የሚቀርበው ጨረታ ዶክመንት፡
- 14.1 ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ሰነድ ለየብቻው አሽጎ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም
- 14.2 ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ሰነድ ለየብቻው አሽጎ ማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል፡፡
- ጽ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ትግራይ መቐለ
ስልክ ቁጥር 0344407335/0914755845
የመቐለ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
ድሕሪት