የጨረታው መስፈርት
1 ተጫራቾች የ2011ዓ/ም የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው :
2 ተጫራቾች ኦርጂናልና የማይመለስ ኣንድ የታደሰ ሊብሬ፣ የኢንሹራንስ መድንና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ በማያያዝ የጨረታው ዝርዝር ሰነድ በስራ ሰኣት ከመቐለ ዋና መ/ቤት ወይም ኣ/ኣበባ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት መውሰድ ይችላሉ።
3 ተጫራቾች የጨረታው ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ 08/04/2019 እ.አ.አ ጀምሮ እስከ 30/04/2019 እ.ኤ.አ ከሰኣት በኃላ 8:00 ሰዓት ጀምሮ መቐለ ዋና መስሪያ ቤት ለዚህ ተብሎ በታዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) 10000.00 /ኣስር ሺ ብር/ በስም በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ጋር ማስገባት አለባቸው :: በፖስታ ያልታሸገ ሲፒኦ እንዲሁም ጥሬ ገንዘብ ተቀባይነት የለዉም።
5 ጨረታዉ 30/04/2019 እ.አ.ኣ ከሰኣት በ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በ 30/04/2019 እ.ኤ.አ ከሰኣት በኃላ 8:30 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በመቐለ መስፍን ዋና መ/ቤት በሚገኝ የስብስባ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸዉ የተሞላ ከሆነ ባይገኙም ጨረታ ሰነዱ ይከፈታል።
6 ተጫራቾቸ የሚያስገቡት ዋጋ ለመኪናው የሚያስፈልገውና ነዳጅና ሌሎች ወጪዎች ያጠቃለለ መሆን ኣለበት፡፡
7 ኣሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ 05 ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ብር 15000.00 ሺ ብር ሲፒኦ በማሰራት ከኩባንያው ጋር ውል መፈራረም ኣለባቸው። ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ ኣማራጭ ይወስዳል።
8 ኣሸናፊው ተጫራች ጨረታው ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ ለስድስት/06/ ወር ውል ያስራሉ፡፡
9 ተጫራቾች ጨረታውን ኣሸንፈው ውል ካሰሩ ቀን ጀምሮ ስራዎን መጀመር ኣለባቸው። ይህ ካልሆነ ግን የውል ማስከበሪያ ያስያዙት ብር ድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅታችን ሌላ ኣማራጭ ይወስዳል፡፡
10 ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ተመስርተው ዋጋ ማስገባት ኣይፈቀድም፡፡
11 ኣሸናፊ ተጫራቾች ድርጅቱ ተጨማሪ መኪና በሚያስፈልግበት ግዜ ባሸነፉት ዋጋ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
12 ኩባንያዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በክፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ:
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁጥር መቐለ +251 0344-406803/6225 ፋክስ 00251 344406225
ኣዲስ ኣበባ ስ.ቁጥር +251-114709792/+251-116298560 መደወል ይቻላል፡፡
ድሕሪት