ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ነገሮች
1 ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከመጋት 13 ቀን 2011ዓ/ም እስከ መጋቢት 23 ቀን 2011ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ መቐለ ከዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 403 በመምጣት የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
2 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ዕቃዎቹ በሚገኙበት ቦተ ኣዋሽ የእህል መጋዘን ኣጠገብ በሚገኘው ጋራዝ ግቢ ውስጥ /ኣዋሽ የእህል መጋዘን ኣካባቢ ሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም ግቢ በኣካል እየቀረቡ ማየት ይችላሉ፡፡
3 ተጫራቾች ለሁሉም ዓይነት በሙሉ ያገለገሉ ወረቀት፣ ባትሪዎች፣ ጎማዎች፣ ፒቪሲ እና የእንጨት ምሰሶ መጫረት ይችላሉ፡፡
4 ተጫራቾች ኣስፈላጊውን የመወዳደሪያ ሰነዶችን በፖስታ ኣሽገው ማስገባት ያለባቸው ከ 13/07/2011 ዓ/ም እስከ 23/07/2011ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡ ከነዚህ ቀናት ሰዓታት በኃላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
5 ጨረታዉ ፍላጎት ያላቸዉ ተጫረቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት 23/07/2011 ዓ/ም ከቀኑ 8:15 ሰዓት ይከፈታል።
6 ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ያቀረቡትን ዋጋ ለመለወጥ ወይም ማሻሻል ኣይችሉም፡፡
7 የጨረታው ውጤት ሳይታወቅ ውድድሩን ማቋረጥ የሚፈልግ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
8 የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና ያላቀረበ ተጫራች ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
9 መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፤
ድሕሪት