በመቐለ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅና ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ለ2007 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚዉሉ አልሙኒየም ፓኔል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ ለማሰራት/ይፈልጋል
በዚሁ መሰረት
1 በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማሰረጃ ማቅረብ የሚችል
2 የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ወይም በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብሳይት የተመዘገበ
3 በቀረበዉ ዝርዝር መግለጫ /ስፔሲፊኬሽን/ መሰረት መስራት የሚችል
4 የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆነ
5 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የሚያቀርብ
6 በኮሌጁ ስም የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 40,000.00 ማስያዝ የሚችልና ላለማጭበርበር በድርጅቱ ስም ቃለ ማሃላ ማቅረብ የሚችል
7 ማንኛዉም ተጫራቾች የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀዉ የጨረታ ሰነድ መዉሰድ ይችላል
8 ማንኛዉም ተጫራች ለዚሁ ጨረታ ተብሎ የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ከመቐለ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዓይደር ግቢ በግ/ን/ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ መዉሰድ ይችላል
9 ጨረታዉ አየር ላይ የሚቆየዉ ጊዜ ጋዜጣዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስክ 15ኛዉ ቀን ከሰዓት 9:30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ያለባቸዉ ሲሆን 15ኛዉ ቀን ከሰዓት 9:30 ሰዓት ተዘግቶ 10:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ራሳቸዉ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል በ15 ቀን በዓል ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል
10 ጨረታዉ አሸንፎ በወቅቱ ዉል ለማያስር የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስለትም
11 ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ
12 ላለማጭበርበር በኮሌጁ ስም ቃለ መሃላ ማቅረብ የሚችል
ድሕሪት