በትግራይ ክልል ዞን ሰ/ምዕራብ ከተማ ሽራሮ ማዘጋጃ ቤት የተለያዩ የልማት ስራዎች ግልጋሎት የሚውል ሎደር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፡-
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቫት ዲክለር፣ የቲን የምዝገባ፣ የዕቃው አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን መጠን በሲፒኦ ወይም አንኮንዲሽናል ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችል።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ብር 100.00 የማይመለስ በመክፈል ከትግራይ ክልል መንገድ ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ መቐለ ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ ለተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ወይም በፖ.ሣ.ቁ. 14 መላክ ይችላሉ።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነው ተወዳዳሪ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሰርቲፋይድ ቼክ (CPO) ወይም Unconditional Bank Guarantee በመያዝ በግንባር ቀርበው ውል መፈፀም የሚችሉ።
- ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይሸጋገራል።
- በጨረታው አከፋፈት ስነ-ስርዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙ ይመረጣል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ድሕሪት