በመቐለ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ፅ/ቤት ተይዘውና ተወርሰው የሚገኙ የተለያዩ አልባሳት ፣ ኤልቲ ዘይድ ብረት እና ባለ 12 ቴንዲኖ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታ እና መስፈርቶችን ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጡ ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው ንግድ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርቲፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑ/በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ/ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የግልፅ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ አስከ ዓርብ እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በፅ/ቤታችን የዕለት ገቢ ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር 7 በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
- በጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ከሚሰጡት ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና c.p.o በመቐለ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ጨረታው ሚካሄደው በመቐለ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ሲሆን በማስታወቂያው በተገለፀው ጊዜ እና ቦታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ተኛ ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ የዕቃዎች ናሙና ወደ መጋዘኑ እየሄዱ መመልከት አለባቸው።
- ጨረታ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ተኛ ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡00 (ሶስት ሰዓት) ተዘግቶ 3፡30 ሰዓት (ሰሶት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ) ይከፈታል።
- ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለፀው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ተኛ የስራ ቀን ሳይሆን ሲቀር ጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
- በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከከፈሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸነፉት ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት ከተገለፀው በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።
- ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታ ማሰከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለፅ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
- ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0910 46 73 76 ወይም
በስልክ ቁጥር 0920 40 05 27 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የመቐለ ቅ/ፅ/ቤት
ድሕሪት