ጨረታዉ በኣዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበት ቀን 4/2/2012
: ጨረታዉ ሚዘጋበት ቀን በ16ኛዉ በ 3:45 ሰዓት
ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን በ16ኛዉ በ4:00 ሰዓት
1 ጨረታው በተመለከተ ንግድ ፍቃድ ያለውና የ2011 ዓ.ም ያሳደሰ መሆን አለበት።
2 በአቅራቢነት የተመዘገበና ቲን ቁጥር ያለው።
3 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺ ብር) በCPO ወይም የግዢ መምሪያ በሚፈቅደው መሰረት ማቅረብ ይጠበቅበታል ።
4 ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት መቐለ ከሚገኘው ከትግራይ ክልል ትምቢሮ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
5 ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በትግራይ ክልል ትም/ቢሮ 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የጨረታ ዶክመንት ማስገባት ይገባል።
6 ጨረታው በ16ኛው ቀን በ 3፡45 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን በዓል ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን የመዝጊያና የመከፈቻ ቀን ይሆናል።
7 የጨረታ አሸናፊ ውል ከፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ 60 ቀናት ውስጥ በተሰጠው ስፔስፍኬሽን መሰረት ጥራት ያለው መፅሃፍት አሳትሞ ትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎች ሸፍኖ በትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርበታል።
8 ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
9 ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0344 40 34 77/0344408299 በመደወል መጠየቅ ወይም በትግራይ
ክልል ትም/ት ቢሮ ዌብሳይት WWW.tigrayeduc.com ማየት ይቻላል።
የትግራይ ክልል ትም/ት ቢሮ