ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 04/2011

የትግራይ ክልል መንገድ ስራዎች ኢንተርፕራይዝ በ2011 በጀት ዓመት ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ አገልግሎት የሚውሉ

  • የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣
  • የፅዳት እቃዎች፣
  • የፅህፈት መሳሪያ /እስቴሽነሪ/
  • የማሽን /መሳሪያ/ ኪራይ /
  • ኤሌክትሮኒክስ እና
  • የቅየሳ መሳሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

  1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የወቅቱን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ፣ የቲን ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን መጠን በሲፒኦ ወይም አንኮንዲሽናል ባንክ ጋራንቲ (unconditional Bank guarantee) ማስያዝ የሚችል፣
  3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ብር 50.00 እና 100.00 ብር በመክፈል ከኢንተርፕራይዙ ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት መውሰድ ይችላሉ፣
  4. የጨረታው ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ወይም በፖ.ሳ.ቁ 14 መላክ ይቻላል።
  5. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ተወዳዳሪ ማሸነፉ በዴብዳቤ ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት  በግንባር ቀርበው ውል ማሰር አለባቸው።
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተወዳዳሪ በዚህ ጨረታ መመሪያ የተዘረዘሩትን ለማሟላት ፍቃደኛ ካልሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ከጨረታው ይሰረዛል።
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል፣ ይሁንና 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፣
  8. በጨረታው አከፋፈት ስነ-ስርዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢኖሩ ይመረጣል።
  9. ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

    ለተጨማሪ ማብራሪያ

    በስልክ ቁጥር 0344-416727/0914734474 መጠየቅ ይቻላል።

የትግራይ ክልል መንገድ ስራዎች ኢንተርፕራይዝ

መቐለ