የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃላ.የተወ.የግል ኩባንያ (SWEI ኢንድስትሪ) ከታች የተለያዪ የፅሕፈት መሳርያዎች እና የፅዳት መሳርያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ ኩባንያችን ይጋብዛል።

የጨረታ መስፈርት

1. ተጫራቾች በዘርፉ የ2017 ዓ/ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የወሩ ቫት ማሳወቅያ ፎቶ ኮፒ በማያያዝ ከጨረታው ዝርዝር (ሰነድ) ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የወሩ ቫት ማሳወቅያ ፎቶ ኮፒ የማይመለስ እና ኦርጅናል የሚመለስ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከቀን ከ 09/12/2024 እ.ኤ.አ ጀምሮ እስከ 23/12/2024 እ.ኤ.አ መቐለ ላጪ ቅርንጫፍ FSWEI ኢንድስትሪ በስራ ሰኣት መወሰድ ይኖርባቸዋል።

3. ጨረታው 23/12/2024 እ.ኤ.አ ከቀኑ 8:00 ሰኣት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከሰኣት 8:30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት መቐለ ዋና መስርያ ቤት በሚገኝ FSWEI ኢንድስትሪ ሳፕላይ ቢሮ የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸው የተሟላ ከሆነ ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል።

4. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫት(VAT) ጨምሮ መሆኑና አለመሆኑን በግልፅ መጠቀስ አለበት:: ይህ ካልሆነ ግን ያስገቡት ዋጋ ቫት እንደሚያካትት ተቆጥሮ ይወሰዳል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ ) ብር 25,000.00 (ሃያምስት ሺህ ብር) በታሸገ ፖስታ ከጨረታው ጋር ማስገባት አለባቸው::በፖስታ ያልታሸገ ሲፒኦ ተቀባይነት የለውም።

6. አዲስ አበባ ለሚገኙ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ራሳቸው ወይም በወኪላቸው መቐለ ዋና መስርያ ቤት በሚገኝ ላጪ ቅርንጫፍ FSWEI ኢንድስትሪ ሳፕላይ ቢሮ ማስገባት ይኖርባችዋል።

7. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋ ቫት ጨምሮ 10% የውል ማስከበርያ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank guarantee) በማሰራት ከኩባንያችን ጋር ውል መፈራረም አለባቸው:: ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ይወስዳል።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን አሸንፈው ውል ካሰሩበት ቀን ጀምሮ በ ቀናት ውስጥ እቃው ማስረከብ አለባቸው::ይህ ካልሆነ ግን ለውል ማስከበርያ ያስያዙት ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ይወስዳል።

9. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ተመስርተው ́ዋጋ ማስገባት አይፈቀድም።

10. ተጫራቾች ይህን ጨረታ ካሸነፉ ለሌላ ሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት አይችሉም::

11. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉት እቃ መቐለ ዋና መስርያ ቤት ድረስ መጥተው ማስረከብ አለባቸው:: ክፍያ በተመለከተ ያቀረቡት እቃ ድርጅታችን ጥራት ቁጥጥር ባለሙያ ተፈትሾ ተቀባይነት ካገኘ በኃላ በ10 ቀናት ውስጥ የሚፈፀም ይሆናል።

12. የእቃው ዝርዝር ሰነድ ከዚሁ ጋር በ ግዢ ሰነድ ቁጥር 462701 እና 462703 ይገኛል::

13. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

መቐለአዲስ-አበባ
ስልክ-+251914702481
ፋክስ-+251-344406225
ስልክ-+251-914726541
ፋክስ-+251-114709636