ግልፅ የውጭ ኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ

ሰሜን ኣነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ኣክስዮን ማህበር ለ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት የተቋሙ የስራ እንቅስቃሴ ወይም የሒሳብ ስራ በውጭ ኦዲተሮች በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል። የሚከተለው መስፈርት የምታሟሉ የኦዲት ተቋማት/Audit Firms/ እንድትወዳደሩ ተቋማችን ይጋብዛል።

1. ተጫራች ከ "Accounting and Auditing Board of Ethiopia (AABE)" ፈቃድ የተሰጠው እና የ2017 ዓ/ም ንግድ ፍቃድ ያሳደሰ መሆን ያለበት ሲሆን ሻት ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃዎች መቅረብ የሚችል፣

2. የተጫራች ሁሉም የኦዲት ቡድን አባላት የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርቲንግ ስታንዳርድ (IRS) እውቀት ያላቸውና በIFRS የሰለጠኑበት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የኦዲት ስራ ኣስኪያጅ (Audit Manager) በፋይናንስ ተቋማት በኦዲት ስራዎች ቢያንስ ሶስት ዓመት የስራ ልምድ ያለው ሆኖ ሌሎች የኦዲት ቡዱኑ ኣባላት በባንክና ማይክሮፋይናንስ ዘርፍ ሰፊና ውስብስብ ስራ ባላቸው የፋይናንስ ተቋማት ኦዲት በማድረግ በቂ ልምድ ያላቸው መሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣

4. የተጫራቾ የኦዲት ቡድን አባላት በፍትሃዊ የዋጋ ኣተማመን (fair value estimation) በቂ እውቀትና የመረዳት ችሎታ ያላቸውና ስልጠና የወሰዱ፣ የሃብትና እዳ ፍትሃዊ ዋጋ ለመወሰን የተተገበሩ ሂደቶች ትክክለኛነት ማረጋገጥ የሚችሉና ማይክሮፋናንስ ተቋሙ በዋጋ ኣተማመን ላይ የተጠቀመባቸው ዋና ታሳቢዎች እና ግብኣቶች የመገምገም ችሎታ ያላችው፣

5. የኦዲት ስራው ሚዛናዊነት፣ ነፃነትና ውጤታማነት ለመጠበቅ ሲባል የተጫራች የኦዲት ቡድን ኣባላት ባለፉት ሶስት ዓመታት የማይክሮፋይናንስ ተቋሙ ሰራኞች ያልነበሩ መሆን አለባቸው፣

6. ተጫራች የውጭ ኦዲተር፣ የውጭ ኦዲተሩ የስራ አጋር ወይም የሰራተኞች ኣባላት የሚከተሉትን የስነምግባር መግለጫ ማረጋገጥ አለበት፡

ሀ. የሰሜን ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኣ/ ባለአክስዮን፣ ዳይሬክተር ወይም ሰራተኛ አለመሆናቸው፣

ለ. የሰሜን ማይክሮፋይናንስ ተቋም ባለኣክስዮን፣ ዳይረክተር ወይም ሰራተኛ የትዳር ጓደኛ ወይም የመጀመርያ ደረጃ ዝምድና ያላቸው ኣለመሆናቸው

ሐ. የኦዲት ተቋሙ ባለኣክስዮን፣ ዳይረክተር ወይም ሰራተኛ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ

i. በሰሜን ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኣ/ማ ባለኣክስዮን፣ ዳይረክተር ወይም ሰራተኛ በባለቤትነት ያልተያዘ መሆኑ፣

ii. በሰሜን ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኣ/ማ ባለኣክስዮን፣ ዳይረክተር ወይም ሰራተኛ የትዳር ጓደኛ ወይም በመጀመርያ ደረጃ ዝምድና በባለቤትነት ያልተያዘ መሆኑ፣

መ. የሰሜን ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኣ/ማ _ ወኪል ወይም ለኣክስዮን ማሕበሩ ማንኛውም ዓይነት ኣገልግሎት ኣቅራቢ ኣለመሆኑ፣

7. ተጫራቹ የአዲት ተቋም፣ የኦዲት ተቋሙ የስራ ኣጋር፣ ዳይረክተር፣ ስራ ኣስከያጅ ወይም የቡዱኑ ኣባላት የሚከተሉት ሁኔታዎችን ማረጋገጥ ኣለበት፡-

ሀ. በፍርድ ቤት ኪሳራ የታወጀባጀው ወይም የከሰሩ ኣለመሆናቸው፣

ለ. በማንኛውም የወንጀል ድርጊት፣ በማጭበርበር/በማታለል፣ በገንዘብ ወንጀል ወይም በሌሎች ህገወጥ ተግባራት በፍርድ ቤት ያልተፈረደባቸው መሆናቸው፣

ሐ. በማንኛውም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ወይም በሌላ የገንዘብ ተቋም ውዝፍ አለመሆናቸው እና

መ. የማንኛውም የግብር ግዴታ ውዝፍ አለመሆናቸው፡፡

8. ተጫራች የውጭ ኦዲተር፣ የስራ አጋሮቹ ወይም የኦዲት ቡዱኑ ኣባላት እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው ምንም ዓይነት የተቀማጭ ሒሳብ እንዳማይሰሩና በክንድ ርዝመት ካልሆነ በስተቀር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሰሜን ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኣ/ማ ተበዳሪ ወይም ተጠቃሚ አለመሆናቸው ማረጋገጥ ይገበዋል፣

9. በተጨራቹ የኦዲት ተቋም በባለቤትነት፣ በዳይሬክቶሮችና በስራ አስኪያጆች ላይ በሚኖረው ለውጥ ምክንያት በዚህ መመርያ ላይ የተቀመጠውን መስፈርቶች | ሳይሟላ ቢቀር እንዲሁም በኦዲት ተቋሙ በማናቸውም የኦዲት ቡድኑ ኣባላት ላይ የሚወሰድ ማናቸውም የዲስፕሊን ወይም ህጋዊ እርምጃ ቢኖር ከኦዲት ተቋሙ የሚደረግ ዉል ሊሰረዝ እንደሚችል በግልፅ መታወቅ አለበት፣

10. ኣንድ የውጭ ኦዲተር ለእያንዳንዱ የኦዲት ቡዱኑ ኣባላት ለእያንዳንዱ ቀጠሮ ወይም ዳግም ቀጠሮ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመርያ _ DIRECTIVE NO.MF1/37/2024 በሚያዝዘው መዕረች “የነፃነት ማረጋገጫ (Independence Confirmation)" እና "ተገቢና ትክክለኛ መግለጫ (Fit and Proper Declaration)" ቅፅ በፅሑፍ ሞልቶ ማቅረብ የሚችል።

11. ተጫራች የውጭ ኦዲተር ባለፉት ሁለት ተከታታይ የኦዲት ኮንትራክት ውል (to consecutive terms) በሰሜን ማክሮፋይናንስ ተቋም በኦዲት ስራ ያልተሳተፉ መሆን ኣለበት፣

12. ተጫራች የኦዲት ተቋም ብቁ የሰው ሃይል በማዘጋጀት ስራዉ ከጀመረ በኋላ በኣንድ ወር ወይ ብ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ስራውን ጨርሶ ለኣክስዮን ማህበሩ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፣

13. ተጫራቶች የጨረታው ሰነድ ከሕዳር 9/2017 ዓ/ም ጀምሮ ከሰሜን ማይክሮፋይናንስ ኣነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ኣክስዮን ማህበር ዋና መስሪያቤት በመቐለ ከተማ መሞና ንግድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ፣ ቁጥር 705 ከሚገኘው ፅህፈት ቤታችን ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይቻላል፣

14. ተጫራች የጨረታው ማስከበርያ የሚሆን ከጠቅላላ ዋጋ ከ2% ያላነሰ በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፣

15. የጨረታ ሳጥን ክፍት ሆኖ የሚቆየው ከ ሕዳር 9/2017 ዓ/ም“ ጀምሮ እስከ “ሕዳር 23/2017 ዓ/ም ከጥዋቱ 4፡ዐዐ” ሆኖ የጨረታ ሳጥን በዚህ ቀን ልክ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ጠዋት በ4፡30 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰን ማይክሮፋይናንስ ኣነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ኣክስዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ ቁጥር 704 ይከፈታል። ተጫራቶች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ህጋዊነቱ እስከ ተጠበቀ ድረስ ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል።

16. የጨረታዉ ኣሸናፊ የጨረታዉ ዉጤት ከተገለፀ በኋላ በተከታታይ 7 ቀናት ዉስጥ ወደ ተቋሙ የሰው ሃይልና ንብረት ኣስተዳደር ቀርቦ ዉል ማሰር አለበት፣

17. የጨረታው አሸናፊ የጨረታዉ ዉጤት ከታወቀ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋ 10% unconditional bank guarantee ማስያዝ አለበት፣

18. ድርጅቱ የተሻለ ኣማራጭ ካገኘ ጨረታዉ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ለበለጠ መረጃ በሞባይል ቁጥር +251 91 476 9186 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡