ለምርት አገልግሎት የሚውል Raw Pet coke impoted አወዳድሮ ለመግዛት ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018
ክፍል አንድ
1. መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት የሚጠቀመው 22,000 ሜትሪክ ቶን Raw pet coke imported አቅራቢዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
2. በጨረታው የሚሳተፉ ድርጅቶች Import & Export በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚገልፅ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸው የሚገልፅ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ብር 1,000,000(አንድ ሚሊዮን ብር)በመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሃ/የተ/የግ/ማ ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (cpo) ወይም ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒካል ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተራ ቁጥር 2 ከተጠቀሱት ማስረጃዎች ጋር በማያያዝ የድርጅታቸውን አርማና ማህተም ያለው ደብዳቤ በመፃፍ ለጨረታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች ከዚህ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ጋር አብሮ ከተገለፀው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ያቀርቡትን Raw pet-coke imported በጨረታው ቀን ወይ ከዛ በፊት በራሳቸው ወጪ ለምርመራ ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። (ናሙናው የሚቀርበው መቀሌ በሚገኘው ፋብሪካ ይሆናል።
6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረብያቸውና በተራ ቁጥር 2 እና 3 ላይ የተጠቀሱት ሰነዶችና በተራ ቁጥር 5 የተጠቀሰውን ናሙና (ሳምፕል) እስከ 17/07/2018 ከጠዋቱ 3፡45 ሰአት ድረስ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን መቀሌ በሚገኘው የፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ ቁጥር 115 በሚገኝ የግዥና አቅርቦት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው በእለቱ 17/07/2018 ከጠዋቱ 3፡45 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8. ፋብሪካው ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ +251 344 405 806
ሞባይል +251 912 502 596
ፋስክ+251 344 405 806 /+251 344 410 863
E-mail: procurementmessebocement2026@gmail.com
መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሃ/የተ/የግ/ማ
መቀለ