የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቀሌ ዲስትሪክት ለከዳነ ተከለ እና ዘርኡ አብርሃ ሕ/ሽ/ማሕበር ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የተያዘውን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የተበዳሪው/የመያዣ ሰጪው ስም | የሚሸጠው ንብረት ዓይነት | ሐራጁ የሚከናወንበት ቦታ | የሐራጁ ደረጃ | የሐራጅ መነሻ ዋጋ /በብር | ሐራጁ የሚከናወንበት ቀንና ሰዓት |
ኪዳነ ተከለ እና ዘርኡ አብርሃ ሕ/ስ/ማህበር | NPR71፣35 ኩንታል የሚጭን አይሱዙ ተሽከርካሪ | የኢትዮጵያ ልማት ባንከ መቐለ ዲስትሪከት ቅጥር ግቢ ውስጥ | ሁለተኛ | 590,000.00 | ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00-6፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- ሐራጁ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡
- የሐራጁ አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 (አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፤ በተጠቀሰው ቀን ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- አሸናፊዉ ያስያዘው ገንዘብ ከግዢዉ ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን ፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው የጨረታ አሸናፊው/ ይከፍላል።
- ሐራጁ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ተበዳሪዎች/ አስያዦች እና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተወካዮች በተገኙበት በግልፅ ይከናወናል፡፡
- ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ለሚገኘው የፕሮጀከት ማስታመሚያና ብድር ማገገሚያ ቡድን በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0344-419016 ወይም 0344-407439 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ ተሽከርካሪው በሥራ ሰዓት መጐብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾችን ከቲሙ ጋር በመነጋገር መጐብኘት ይቻላል
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቐስ ዲስትሪክት
Backs