- የህትመት ሥራዎች እና
- የታብሌት ኮምፒዩተሮች ከህጋውያን ነጋዴች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ህጋውያን ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡
- ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) እንዲሁም የታደሰ የአቅራቢች ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የቫት ምዝገባ የምስክር ወረት እና የሚያዝያ 2011 - ዓ.ም. ቫት ዲክሌር ያደረጉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ሎት-1 የህትመት ሥራዎች/ ሲፒኦ/ CPO ብር 20,000 እና ለሎት-2 የታብሌት ኮምፒዩተሮች /ኢፒኦ/ (CPO) ብር 5,000 ማስያዝ የሚችሉ፤
- ተወዳዳሪዎች ለሎት1 [የህትመት ሥራዎች የጨረታን ፋይናንሻል ዶክሜንት አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እንዲሁም ለሎት -2 /የታብሌት ኮምፒዩተሮች ፋይናንስ እና ቴክኒካል ዶክሜንት አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰዓት የግዥ ንኡስ ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር-42 ማስገባት አለባቸው፧
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሆኖ የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መምሪያዎች በሙሉ በሚሸጠው ጨረታ ሰነድ መመልከት ይቻላል፤
- ተወዳዳሪዎች በተሰጠው ዝርዝር ስፔሲፊኬሽን መሰረት የመወዳደሪያ ዋጋቸውን መሙላት ይጠበቅባቸዋል፤
- ተወዳዳሪዎች የሚያስቡት ዋጋ ቫት እና የትራንስፖርት እንዲሁም ሌሎች ወጪዎች ያካተተ መሆን አለበት ካልሆነ እንዳካተተ ይቆጠራል፤
- ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ሆነው ከተገኙ ውል ከገቡበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለሎት-1 /የህትመት ሥራዎች 60 ተከታታይ ቀናት ለሎት-2 /የታብሌት ኮምፒዩተሮች ደግሞ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 100.00 [አንድ መቶ ብር/ ከፍለው ከክልል ትግራይ ጤና ቢሮ የግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 42 በሥራ ሰአት መግዛት ይችላሉ፤
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው እንዲሁም 20% መጨመር አልያም መቀነስ ይችላል፤
- ማንኛውም ግልፅ ያልሆነ ጥያቄ ካላችሁ ጨረታ ሰነድ የሚከፈትበት ቀን ከመድረሱ ከ5 ቀናት በፊት በጽሑፍ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
- ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት (BID VALIDITY DATE) 60 ቀናት ይሆናል፤
- በእያንዳንዱ ንብረት አሸናፊ ይለያል በድምር ወይም በጠቅላላ አሸናፊ አይደረግም፤
ለበለጠ መረጃ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ
ስ.ቁ 03-44-40-47-15፤ ደውለው መጠየኝ ይችላሉ
Backs