መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ኮምፒውተር እና ተዛማች እቃዎች፣ የምግብ ቤት ማሽኖች ጥገና ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ ፣ ጀነሬተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

 መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች እና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና ፍቃዱንም በዘመኑ የታደሰ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚቸል፤

2. በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን እና መስፈርት መሰረት ማቅረብ የሚችል፣

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ምዝገባ ስርተፊኬት ማቅረብ የሚችል

መለያ

የጨረታው አይነት

የጨረታ  ማስከበርያ ብር

ደረጃ

Lot 1

የሠራተኞች ደንብ ልብስ

70,000.00

Lot 2

የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

50,000.00

Lot 3

የኤሌክትሪክ እቃዎች

50,000.00

Lot 4.

ኮምፒውተር እና ተዛማች እቃዎች

50,000.00

Lot 5

የምግብ ቤት ማሽኖች ጥገና ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ

100,000.00

Lot 6

ጀነሬተር

10,000.00

ባንክ የተመሰከረለት (CPO) ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ስም ማሰያዝ የሚችሉ፡፡

4 ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር / በመክፈል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መውሰድይችላል፣

5 ማንኛውም ተጫራች ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳ/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላል፣

6 ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 3:30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

7 ጨረታው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ጠዋት 3:30 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ልክ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣

8 በጨረታው አሸንፎ በወቅቱ ውል ለማያስር የጨረታ አሸናፊ ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ (CPO) አይመለስለትም፣

9 ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው::

ለበለጠ ማብራሪያ፡የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር G21-201 -

ስ.ቁ. 034 41 47 84/09 14 72 74 48፣ ፖ.ሳ.ቁ. 231 ዋና ግቢ

Backs
Tender Category